በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፖሊዮ ክትባት በደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ የስደተኞች ሠፈሮችና አካባቢያቸው ማክሰኞ፣ ግንቦት 27 ይጀመራል


የኢትዮጵያው ዶሎ ኦዶ እና የኬንያው ዳዳብ
የኢትዮጵያው ዶሎ ኦዶ እና የኬንያው ዳዳብ

ደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኘው የዶሎ ኦዶ የስደተኞች መጠለያ ሠፈርና በአካባቢው ባሉ ወረዳዎች ከነገ ግንቦት 27 / 2005 ዓ.ም ጀምሮ የፖሊዮ ክትባት እንደሚሰጥ ተገለፀ፡፡






please wait

No media source currently available

0:00 0:10:50 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ሶማሊያ ውስጥ በቅርቡ ተከሰተ ከተባለውና ወደ ኬንያ ዳዳብ የስደተኞች መጠለያ ወረዳ እንደተዛመተ ከተነገረው አደገኛ የልጅነት ልምሻ ቫይረስ ጋር በተያያዘ ከነገ ግንቦት 27 / 2005 ዓ.ም ጀምሮ ደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኘው የዶሎ ኦዶ የስደተኞች መጠለያ ሠፈርና በአካባቢው ባሉ ወረዳዎች የፖሊዮ ክትባት እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡
ዶሎ ኦዶ
ዶሎ ኦዶ
ይህንን ያሣወቁት የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር - ዩኤንኤችሲአር የኢትዮጵያ ቢሮ ቃልአቀባይ አቶ ክሱት ገብረእግዚአብሔር ናቸው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በግዙፉ የምሥራቅ አፍሪካ የስደተኞች መጠለያ ኮምፕሌክስ - የኬንያው ዳዳብ ውስጥ ታይቷል የተባለውን ይህንኑ የልጅነት ልምሻ ወረርሽኝ እዚያው ለማቆም ያግዛል የተባለ መጠነ ሰፊ ክትባት የመጀመሪያውን ዙር ማጠናቀቁን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል፡፡
ዕድሜአቸው እስከ 15 ዓመት የሚደርስ 288 ሺህ ሕፃናት መከተባቸውን የመንግሥታቱ ድርጅት አካላት የሆኑት የስተደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር - ዩኤንኤችሲአር እና የዓለም የጤና ድርጅት ትናንት ባወጡት የጋራ መግለጫ አመልክተዋል፡፡
በያዝነው ግንቦት የመጀመሪያ ሣምንት ውስጥ የመጀመሪያው የፖሊዮ ምልክት በዳዳብ የመጠለያ ሠፈሮች ውስጥ አራት ሰዎች ለፖሊዮ ቫይረስ መጋለጣቸውን ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል፡፡
ዳዳብ ውስጥ ክትባቱ ላልደረሣቸው ተጨማሪ 424 ሺህ ስደተኞች የሚሰጠው ክትባት በመጭው ሣምንት ውስጥ እንደሚቀጥል የመንግሥታቱ ድርጅት የጤናና የስደተኞች ጉዳይ መርኃግብር መሥሪያ ቤቶች አስታውቀዋል፡፡
የዳዳብ የስደተኞች መጠለያዎች በሚገኙባቸው የሰሜን ምሥራቅ ኬንያ አቅራቢያና አዋሣኝ ቀበሌዎች ነዋሪዎችም ክትባቱ በኬንያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እየተሰጠ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ደቡብ ሶማሊያ ውስጥ ላለፉት ሦስት ዓመታት በርትቶ በቆየው የፀጥታ እጦት ምክንያት የፖሊዮ ክትባት እንቅስቃሴ ተቋርጦ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በሌላ መረጃ ደግሞ በኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ሰሜናዊ ግዛት የኢቦላ ትኩሣት ሊሆን ይችላል የተባለ ወረርሽኝ መቀስቀሱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል፡፡
የሕመሙ ምልክት የታየባቸው ሰዎች የተገኙት ከዩጋንዳ ድንበር 700 ከማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ደግሞ 200 ኬሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አኬቲ ክልል በምንጎ የጤና ቀጣና በሚባል አካባቢ መሆኑ ታውቋል፡፡
ችግሩን በቅድሚያ ባለፈው ሣምንት ውስጥ ያሣወቀው የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ - ኦቻ ሲሆን የምርመራዎቹ ውጤት ይህ ዘገባ ሲጠናቀር እየተጠበቀ እንደነበር ተገልጿል፡፡

ተጨማሪ ጤና ነክ መረጃዎች፡-
ባለፈው ዓርብ፣ ግንቦት 23 የዓለም ፀረ-ትምባሆ ቀን ሆኖ አልፏል፡፡
ትምባሆ ከተጠቃሚዎቹ ግማሽ ያህሉን እንደሚገድል ያውቃሉ?
በትምባሆ ምክንያት በየዓመቱ በዓለም ዙሪያ ስድስት ሚሊየን ሰው እንደሚሞት ያውቃሉ?
ይህ ትምባሆ በየዓመቱ የሚገድለው ሰው ብዛት በመጭዎቹ 15 ዓመታት ውስጥ ስምንት ሚሊየን ይደርሣል ተብሏል፡፡
ከዓለም አጫሾች ወደ ሰማንያ ከመቶ የሚሆኑት የሚኖሩት አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሃገሮች ውስጥ ነው፡፡
የዓለም የትምባሆ አጠቃቀም መጠን በየጊዜው እየጨመረ የመጣ ጉዳይ ነው፡፡
ከዓለም የጤና ድርጅት የተገኘ መረጃ ነው፡፡


በቅርብ ሰሞናት ለዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መምሪያና የሕግ መወሰኛ እንደራሴዎች፣ ለኒው ዮርክ ከንቲባ ማይክል ብሉምበርግ እና ለአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ሬሲን የተባለ መርዝ የተነካኩ ፖስታዎች ደርሰዋቸዋል፡፡
መርዙ ቀድሞ ተደርሶበታል፤ ኤንቨሎፖቹ በእጃቸው ያለፈ ሲቪል ሠራተኞችም ችግር እንዳልገጠማቸው ተገልጿል፡፡
ሬሲን የመግደል አቅሙ ከፍተኛ የሆነ መርዝ ነው፡፡
ሬሲን የሚወጣው ከጉሎ ፍሬ ዘይት ለመጭመቅ በሚደረግ ሂደት ውስጥ ነው፡፡
በዱቄት መልክ ወይም በብናኝ ወይም ትነት፣ ወይም በእንክብል መልክ ሊቀርብ ይችላል፡፡
አንድ ሰው ለሬሲን በተጋለጠ በ36 ሰዓታት ውስጥ ሊሞት ይችላል፡፡
ሬሲን መርዝ ማርከሻ የለውም፡፡
ሬሲን በቆዳ ውስጥ ሰርጎ ወደሰውነት አይገባም፡፡
ከአሜሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከላት - ሲዲሲ የተገኘ መረጃ ነው፡፡

እራስዎንና ቤተሰብዎን ይጠብቁ
እራስዎንና ቤተሰብዎን ይጠብቁ

እባክዎ ጤናዎን ይጠብቁ፤ የግል ንፅህናዎን፣ የቤተሰብዎን ንፅህና፣ የቤትዎንና የአካባቢዎን ፅዳት ይጠብቁ፡፡ ለበሽታ ቀን አይስጡ፡፡ ካመመዎ፤ በኋላ፣ ነገ፣ ከነገ ወዲያ አይበሉ፡፡ አሁኑኑ ብድግ ይበሉና ቅርብዎ ያለ የጤና ባለሙያ ዘንድ ሄደው ያማክሩ፡፡
ከቪኦኤ አፍሪካ የጤና አውታር
ለተጨማሪ መረጃ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG