በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካዊው ኣቃቢ ህግ እና ባለቤታቸው ከኢትዮጵያ በጉዲፈቻ ባመጧቸው ህፃናት ላይ ከባድ ጥቃት በማድረስ ተከሰሱ


ፔንሲልቬንያ ስቴት /በጥቁር የተሠመረው ግዛቲቱ የት እንደምትገኝ በግምት ለማመላከት የተቀመጠ እንጂ ኦፌሴላዊ ክልል አይደለም/
ፔንሲልቬንያ ስቴት /በጥቁር የተሠመረው ግዛቲቱ የት እንደምትገኝ በግምት ለማመላከት የተቀመጠ እንጂ ኦፌሴላዊ ክልል አይደለም/

ዳግላስ ባርበር እና ባለቤታቸው ክሪስቲን ባርበር ባለፈው መጋቢት ከኢትዮጵያ በጉዲፈቻ ባመጧቸው ህፃናት ላይ “ከባድ ጥቃት አድርሰዋል” ተብለው ተከስሰዋል፡፡


please wait

No media source currently available

0:00 0:09:48 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ



ዳግላስ ባርበር በዩናይትድ ስቴትስ ፔንሲልቬንያ ክፍለ ሀገር ውስጥ ታዋቂ የሆኑ ምክትል ጠቅላይ ኣቃቢ ህግ ናቸው፡፡
የስድስት ዓመቱ ወንድ ልጅ ምግብ ለረጅም ጊዜ ከመከልከሉና ከሌላም አካላዊ ጥቃት የተነሳ ሰውነቱ ከስቶና ተጎድቶ ሆስፒታል ገብቷል፡፡ ሴቷ የዓመት ተመንፈቅ ልጅ ደግሞ በርካታ የአጥንት ስብራት የተገኘባት ሲሆን ዓይኖቿ ላይም ዘላቂ ለሆነ ብርሃን ማጣት ሊዳርጋት ይችላል ብለው ሐኪሞች የሰጉበት ጉዳት ደርሶባታል።
ተከሳሾቹ በጥቂት ቀናት ውስጥ ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ሲሆን በዋስ ተለቅቀዋል።
የህፃናቱን ሁኔታ ባዩበት ወቅት ይህ የከፋ ጥቃት ምልክት እንጂ ወትሮ በልጅ ላይ የሚታይ ህመም አይደለም ብለው ካስጠነቀቁት መካከል አንዲቱ ሐኪም ጉዳዩ ገና በክሥ ሂደት ላይ ያለ ስለሆነ ዝርዝር ውስጥ ሊገቡ እንደማይችሉ አስቀድመው ካሣወቁን በኋላ ልጆቹ ባሁኑ ጊዜ በደህና ሁኔታ ላይ ናቸው፤ የሚያሰጋ ነገር የለም ብለዋል።
የት ናቸው ለሚለው ጥያቄ ግን እዚህ ቦታ ማለት እንደማይችሉ ፣ ነገር ግን ያሉበት የማያሰጋ ቦታ ነው ብለው አጠቃለውታል።
ወይዘሮ ለምለም ፀጋው ከጥቂት ወራት በፊት የተመሠረተው የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል መሥራችና የአመራር አባል ናቸው። “ጉዳዩ የሚሰቀጥጥ ነው፤ እኛም ምን መደረግ አለበት የሚለውን እየተነጋገርንበት ነው” ብለዋል ። “በጉዲፈቻ ከኢትዮጵያ ወደያገሩ የሚወሰዱ ህፃናት ደህንነት ሁላችንንም የሚመለከት ቢሆንም ከየአገሩ የህፃናት ደህንነት አስጠባቂ ተቋማት ጋር ግንኙነት መሥርቶ ደህንነታቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት ግን በየአገሩ ያለው የኢትዮጵያ መንግሥት ኤምባሲ ወይም ቆንስላ መሆኑ ግልፅ ነው ብለዋል።”
ዝርዝሩን ያዳምጡ
XS
SM
MD
LG