በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዋጋዱጉ - ቡርኪና ፋሶ ውስጥ አደጋ ተጣለ


ስፕሌንድድ ሆቴል ዋጋዱጉ
ስፕሌንድድ ሆቴል ዋጋዱጉ

ቡርኪና ፋሶ ዋና ከተማ ዋጋዱጉ ውስጥ በውጭ ዜጎች በሚዘወተር “ስፕለንዲድ” በሚባል ሆቴል ላይ ታጣቂዎች ተኩስ ከፈቱ፡፡

ቡርኪና ፋሶ ዋና ከተማ ዋጋዱጉ ውስጥ በውጭ ዜጎች በሚዘወተር “ስፕለንዲድ” በሚባል ሆቴል ላይ ታጣቂዎች ተኩስ ከፈቱ፡፡

በሆቴሉ አጠገብ በሚገኝ “ሎ ካፑቺኖ” በሚባል ሻይ ቤት ውስጥም ተመሣሣይ ጥቃት መፈፀሙ ተዘግቧል፡፡

ሦስት ታጣቂዎች በሆቴሉ ላይ ከተፍተውታል በተባለው ተኩስ ሆቴሉ መቃጠሉም ተገልጿል፡፡

አንድ በሥፍራው የነበረ የዐይን እማኝ ለቪኦኤ ሪፖርተር ሲናገር “ተኩስ ሰማሁ፤ ፈጥኜ ወደ በረንዳ ስሄድ ጠብመንጃ የያዘ ብዙ ሰው ሲሯሯጥ አየሁ፡፡ ከዚያም ተደበቅኩኝ፡፡ እዚያ ሆነን ብዙ ተኩስ ሰማን፡፡ እንደእውነቱ ከባድ መሣሪያ መሆን አለበት፡፡ ምግብ ቤቱ ውስጥ ያሉት ተጠቃሚዎች ሕንፃውን ለቅቀው እንዲወጡና መሬት ላይ እንዲተኙ አዘዟቸው፡፡ ከዚያም ክዋሜ ን’ኩርማህ ጎዳና ወደሚገኘው ስፕሌንዲድ ሆቴል ሄዱና ተኩስ ከፈቱ፡፡ የተወሰኑ ሰዎችን ሳያግቱ አልቀሩም፡፡ አንዳንድ ጉዳትም የደረሰ ይመስለኛል” ብሏል፡፡

ዋጋዱጉ ውስጥ ከሚገኙት ትላልቅ ሆቴሎች አንዱ በሆነውና ብዙ ጊዜ ምዕራባዊያንና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሠራተኞች በሚያዘወትሩት ስፕሌንዲድ ሆቴል ላይ አደጋው ከተጣለ በኋላ ወትሮ ደማቅ የነበረው የከተማይቱ እምብርት መንገዶች ሙሉ በሙሉ ባዶ መሆናቸውንና መኪና ስትቃጠል ማየቱን እዚያው የሚገኝ አንድ የፈረንሣይ የዜና ወኪል ሪፖርተር ተናግሯል፡፡

የፀጥታ ጥበቃ ኃይሎች ገና ወደአካባቢው አለመድረሣቸውንም ሪፖርተሩ ገልጿል፡፡

ጥቃቱን ያደረሱት የአካባቢውን የባሕል ልብስ የለበሱ ሦስት ታጣቂዎች መሆናቸውን ሪፖርተሩ ከመግለፁ በስተቀር ጥቃቱ የማን አድራጎት እንደሆነ ገና አልታወቀም፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የቪድዮ ፋይል ይመልከቱ፡፡

ዋጋዱጉ - ቡርኪና ፋሶ ውስጥ አደጋ ተጣለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:23 0:00

XS
SM
MD
LG