በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዘንድሮ ከሚሊዮን በላይ ስደተኛ አውሮፓ ገባ


እየተጠናቀቀ ባለው የአውሮፓ 2015 ዓ.ም ወደ አውሮፓ የገባው ፍልሰተኛ ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን መብለጡን ዓለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት - አይኦኤምና የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሺነር - ዩኤንኤችሲአር አስታውቀዋል፡፡

ስደተኞችና ፍልሰተኞች በሜዲትራንያን
ስደተኞችና ፍልሰተኞች በሜዲትራንያን

መደበኛ ያልሆኑ የየብስ እና የባሕር ላይ ጉዞዎችን ጨምሮ ከአፍሪካና ከመካከለኛው ምሥራቅ ወደ አውሮፓ የገባው ሰው ባለፈው ዓመት ከነበረው ከአራት እጥፍ እንደሚልቅ ተገልጿል፡፡ይህ ቁጥር ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ግዙፉ የፍልሰትና የስደት ቁጥር መሆኑን አይኦኤም አመልክቷል።

አንድ ሚሊየን አምስት መሺ 504 ሰው ነው ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ታኅሣስ 22/2008 ዓ.ም ወደ አውሮፓ እንደገባ አይኦኤም ያስታወቀው።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:03:58 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG