በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦሕዴድ ከ120 በላይ አባላቱን በሙስና ጠርጥሮ አገደ


አብዛኞቹ ታሳሪዎች በአዲስ አበባና ናዝሬት አካባቢ የሚገኙ መሬቶችን ለግል ጥቅማቸው በመሸጥ ተጠርጥረዋል።
አብዛኞቹ ታሳሪዎች በአዲስ አበባና ናዝሬት አካባቢ የሚገኙ መሬቶችን ለግል ጥቅማቸው በመሸጥ ተጠርጥረዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በክልሉ ማረሚያቤቶች ያለ ጠያቂ በእስር ላይ ናቸው

ከአንድ ሳምንት በላይ የፈጀው የኦሕዴድ ድርጅታዊ ግምገማ ከ120 በላይ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ባለስልጣናትን የሙስና ጉዳይ መርምሯል።

በአሁኑ ወቅት በክልሉ ማረሚያ ቤቶች ቁጥጥር ስር የሚገኙት ባለስልጣናት ከሃላፊነታቸው እንዲነሱና ለፍርድ እንዲቀርቡ መወሰኑን በስብሰባው የተሳተፉና መግለጫ የመስጠት ስልጣን የሌላቸው የኦሕዴድ አባላት ገልጸውልናል።

ከታሳሪዎቹ የሚበዙት በከተማ ከንቲባነትና በቀበሌ አስተዳድር ውስጥ የሚሰሩ ቢሆኑም የክልሉ ካቢኔ አባላት የነበሩ ከፍተኛ አመራሮችም እንደሚገኙበት ታውቋል።

በተለይ በሰበታ፣ አለምገና ናዝሬት (አዳማ) ደብረ ዘይት (ቢሾፍቱና) በጠቅላላው በአዲስ አበባና በአካባቢዋ የሚገኙ ከተሞች ሹማምንት በሙስና ተጠርጥረው ከታሰሩት የሚበዙት ናቸው።

ከህዝብን መሬት ለባላሃብቶችና ለግለሰቦች፤ በጥቅም በመደለል የሚዘርፉ ባለስልጣናት መበራከታቸውን ጠንቅቀው እንደሚያውቁ፤ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሳምንቱ መጨረሻ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አብራርተዋል።

“መሬት የዘረፉም ያልዘረፉም ሰዎች እንዳሉ እናውቃለን። ዋናው አደጋ ዘራፊው ሳይሆን አዘራፊው ነው” ብልዋል አቶ መለስ። መሬት ከዘረፉት ባለሃብቶች ጥቂቶቹ ለፍርድ እንደሚቀርቡና የተቀሩት ደግሞ ምህረት ተደርጎላቸው በከባድ አስተዳድራዊ ቅጣት ይቅርታ እንደሚደረግላቸው ተናግረዋል።

“ያዘረፉት የመንግስት ሰራተኖች በሙሉ ግን፤ በሙሉ ፍርድ ቤት ይሄዳሉ። ትልቁ አደጋ የመንግስት ሙስና ነው።

በናዝሬት ከተማ ለረጂም ጊዜ የኖረውና ሙሉ ስሙን እንዳንጠቅስ የጠየቀን ነዋሪ በኦሮሚያ ክልል፤ በተለይ በናዝሬት የሙስና ችግር አዲስ አይደለም ይላል።

መንግስት እያወቀ፤ ህዝቡን የቀበሌ ሹማምንት፣ የከተማ ከንቲባዎች መሬቱን እየሸጡ፣ ከቤቱ እያፈናቀሉ ሲያጎሳቁሉት፤ መንግስት የት ነበር? ብሎ ይጠይቃል የናዝሬቱ ነዋሪ።

ነዋሪው የሚናገረው መንግስት ሁኔታውን ላለፉት አምስት አመታት ጠንቅቆ እንደሚያውቀው ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሙስና ኢህ አዴግ በምርጫው ወቅት ከህዝቡ ከተጠቆሙ ድክመቶቹ አንዱ መሆኑን ያምናሉ። በኦሮሚያ ምክር ቤት የተካሄደውን ስብሰባ የመሩት የክልሉ ፕሬዝደንት አቶ አለማየሁ አቶምሳን የአዲስ አበባው ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ ናቸው።

XS
SM
MD
LG