በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ድርጅት ባወጣው መግለጫ፣ በኦሮሚያ ወደ 140 የሚሆኑ ሰዎች መሞታቸውን ይገልጻል


የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ድርጅት (Human Rights Watch)
የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ድርጅት (Human Rights Watch)

የሰብአዊ መብት ድርጅቱ በመግለጫው የጠቀሰው አኃዝ፣ እስካሁን መንግሥት ካረጋገጠው ቁጥር ሆነም ሌሎች የመብት ተሟጋች ድርጅቶች ከዚህ በፊት ከጠቀሱት ቁጥር በእጅጉ የላቀ ነው። መንግሥት ግን በዚህ ሰልፍ ምክንያት የ5 ሰዎችን ሞት ብቻ ነው እስካሁን ድረስ ያመነው።

በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ከ8 ሳምንታት በላይ እየተካሄዱ ባሉት የኦሮምያ ክልል ተቃውሞ ሰልፎች፣ በክልሉ በትንሹ ወደ 140 የሚደርሱ ሰዎች መሞታቸውን፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ዛሬ ዐርብ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅት (Human Rights Watch) ገልጸዋል።

የሰብአዊ መብት ድርጅቱ በመግለጫው የጠቀሰው አኃዝ፣ እስካሁን መንግሥት ካረጋገጠው ቁጥር ሆነም ሌሎች የመብት ተሟጋች ድርጅቶች ከዚህ በፊት ከጠቀሱት ቁጥር በእጅጉ የላቀ ነው።

የድረጅቱ የአፊርካ ቀንድ፣ ማለትም በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ጥናት የሚያካሄዱ ቃል-አቀባይ ፊሊክስ ሆርን (Felix Horne) ስለየሟቾቹ ቁጥር እርግጠኛ ግምት ማግኘት እንዳልተቻለም ለቪኦኤ ገልጸዋል።

ይህ የ140 ሰዎች መሞት እናም በተጨማሪ ሌሎች አያሌ የመንግሥት ተቃዋሚዎች መቁሰል፣ እአአ ከ2005ቱ ምርጫ እና እአአ ከ2014ቱ በክልሉ የተደረጉ ሰልፎች ወዲህ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የተካሄደ ትልቁ አመጽ ነው ብለዋል። መንግሥት ግን በዚህ ሰልፍ ምክንያት የ5 ሰዎችን ሞት ብቻ ነው እስካሁን ድረስ ያመነው። ሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፣ ጋዜጥኞች፣ ተማሪዎችና ተራ ዜጎች መታሰራቸው እንዳሳሰባቸው አስረድተዋል።

የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅት (Human Rights Watch) የአፊርካ ቀንድ፣ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ጥናት የሚያካሄዱ ቃል-አቀባይ ፊሊክስ ሆርን (Felix Horne)
የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅት (Human Rights Watch) የአፊርካ ቀንድ፣ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ጥናት የሚያካሄዱ ቃል-አቀባይ ፊሊክስ ሆርን (Felix Horne)

ፊሊክስ ሆርን ዛሬ በሰጡት ቃል፣ የኢትዮጵያ ፀጥታ አስከባሪዎች፣ ተቃዋሚዎቹ ብሶታቸውን በሰላማዊ መንገድ ለማሰማት የሚንቀሳቀሱባቸውን መንገዶች በመዝጋት፣ የጭካኔ እርምጃ እንደወሰዱባቸው ገልጸዋል። ዘላቂ መፍትሄው ግን፣ የኢትዮጵያ መንግስት ከኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት ጋር ቁጭ ብሎ መነጋገር ሲጀምር ነው ብለዋል።

ከኅዳር ወር አጋማሽ እስካሁን የሚቀጥለው ሂደቱ፣ ኢትዮጵያን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ሊሆን እንደሚችልም ቃል-አቀባዩ ጨምረው ተናግረዋል።

ሰፋ ያለ ዝርዝሩን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።

በኦሮሚያ ወደ 140 የሚሆኑ ሰዎች መሞታቸውን የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ይገልጻሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:53 0:00

XS
SM
MD
LG