በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦሮሚያ ወቅታቂ ሁኔታ


የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ለተቃውሞ ሰልፍ በወጡበት ወቅት የተነሳ ፎቶ[ፋይል - ሮይተርስ]
የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ለተቃውሞ ሰልፍ በወጡበት ወቅት የተነሳ ፎቶ[ፋይል - ሮይተርስ]

እንዳለፈው ጊዜ ግድያውና ግብግቡ ባይኖርም ዛሬም ግን ኦሮሚያ አካባቢ አፈሳና ወከባው ቀጥሏል ይላሉ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኰንግሬስ ዋና ጸሓፊ አቶ በቀለ ነጋ። ሆሮ ጉዱሩ ውስጥ በተለይም አሊቦና ቂረሙ አካባቢ የሕዝቡና የተማሪዎቹ ጥያቄ ቀጥሎ ሰላማዊ ትግሉ እየተካሄደው መሆኑንም ገልጸዋል። አቶ በቀለ አክለውም፣ የኦፌኰ ጥያቄ የመገንጠል ሳይሆን የዴሞክራሲ፣ የሰብዓዊ መብት መከበርና የእኩልነት ጥያቄ እንደሆነም ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት ሰላማዊ ትግሉ በብዙዎቹ የኦሮሚያ ክልሎች እንደቀጠለ መሆኑን የገለጹት አቶ በቀለ ነጋ፣ ሆሩ ጉዱሩ ውስጥ አሊቦ፣ ኪሩሙና እና አሙሩ በተባሉ አካባቢዎች ሕዝቡም ሆነ ተማሪዎቹ እንቅስቃሴ ላይ ናቸው ብለዋል።

በተለይም በፓርቲው አመራሮች ላይ የሚካሄደው እስራት እንደጠለ መሆኑ ተገልጧል። ከታሳሪዎቹ መካከልም፣ ባለፈው 2007 ምርጫ፣ መድረክን ተወክለው የተወዳደሩ እጩዎች እንደሚገኙባቸው አቶ በቀለ አውስተዋል።

ትግሉ ለነፃነት፣ ለእኩልነት፣ ለዴሞክረሲና ለሰብዓዊ መብት መከበር ነበር
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኰንግሬስ ዋና ጸሓፊ አቶ በቀለ ነጋ

"የወቅቱ የኦሮሚያ እንቅስቃሴ በመገንጠል ጥያቄ ላይ ያተኮረ ነው ትባላላችሁ" ተብሎ ለቀረበው ጥያቄም አቶ በቀለ ሲመልሱ፣ ድርጅታችን የመገንጠል ጥያቄ ህገ-መንግሥቱ ውስጥ እንዳለ እያወቀም፣ ትግሉ ግን ለነፃነት፣ ለእኩልነት፣ ለዴሞክረሲና ለሰብዓዊ መብት መከበር ነበር።

ስለዚህ የእኛ ጥያቄ የመገንጠል ጥያቄ አይደለም ብለው፣ ይህ ጥያቄ ግን ከኦሮሞ ሕዝብ ጋር ውይይት የሚደረግበት እንጂ አሁን እንደ አዲስ የሚነሳ ጥያቄ አለመሆኑንም ተናግረዋል።

የኦፌኰ ዋና ጻፊ አቶ በቀለ ነጋ ከአዲሱ አበበ ጋር ያደረጉትን ሙሉ ቃለ ምልልስ፣ የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያድምጡ።

የኦሮሚያ ወቅታቂ ሁኔታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:12 0:00

XS
SM
MD
LG