በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦብነግ የኢትዮጵያን መንግሥት በጭፍጨፋ ከሰሰ


ኦብነግ “የኦጋዴን ብሔራዊ ባንዲራ” የሚለው ባንዲራ /ፎቶ - ከዊኪፔድያ የኢንተርኔት ኢንሳይክሎፔድያ የተገኘ/
ኦብነግ “የኦጋዴን ብሔራዊ ባንዲራ” የሚለው ባንዲራ /ፎቶ - ከዊኪፔድያ የኢንተርኔት ኢንሳይክሎፔድያ የተገኘ/

ሶማሊያ ክልል ውስጥ የመንግሥት ወታደሮችና የክልሉ ልዩ ፖሊስ ጥቃት አድርሰው ሃምሣ አንድ ሰው ገድለዋል ሲል የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ስሞታ አሰምቷል፡፡

ሶማሌ ክልል ውስጥ ጃማ ዱባድ በሚባል መንደር ሰሞኑን የመንግሥት ወታደሮችና የክልሉ ልዩ ፖሊስ ኃይሎች በመንደርተኞች ላይ ጥቃት አድርሰው ሃምሣ አንድ ሰው ገድለዋል ሲል የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጭ ግንባር - ኦብነግ ከስሷል፡፡

“የመንግሥቱ የፀጥታ ኃይሎች በሌሎች አካባቢዎችም በተለያዩ የቅርብ ጊዜያት ከሦስት መቶ በላይ ሰላማዊ ሰዎችን ገድለዋል” ያሉት የኦብነግ ቃል አቀባይ አቶ ሃሰን አብዱላሂ ድርጅታቸው ጉዳዩን ለዓለምአቀፍ ተቋማት ለማድረስ ማስረጃዎችን እያጠናቀረ መሆኑን ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የቪኦኤ የሶማሊኛ ዝግጅት ክፍል ወደ አካባቢው ደውሎ ያነጋገራቸው የጎሣ መሪ ወታደሮቹ ስድስት ሕፃናትና ሴቶችንም ጨምሮ ሃያ አራት ሰዎችን መግደላቸውን አመልክተዋል፡፡ ሌሎች ምንጮች ደግሞ ወታደሮቹ መንደሪቱን ማቃጠላቸውንና አሥር ሰዎች የገበቡበት እንደማይታወቅ ጠቁመዋል፡፡ ስለጉዳዩ ከክልሉም ሆነ ከፌደራል መንግሥቱ የተሰጠ መግለጫ የለም፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ኦብነግ የኢትዮጵያን መንግሥት በጭፍጨፋ ከሰሰ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:42 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG