በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕረዚደንት ኦባማ ለኢትዮጵያ ድርቅ አገራቸው እና ካናዳ እርዳታ እየሰጡ ነው አሉ


ፕረዚደንት ኦባማ ለኢትዮጵያ ድርቅ አገራቸው እና ካናዳ እርዳታ እየሰጡ ነው አሉ - ቪድዮ 2
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:43 0:00

ፕረዚደንት ኦባማ ለኢትዮጵያ ድርቅ አገራቸው እና ካናዳ እርዳታ እየሰጡ ነው አሉ - ቪድዮ 2

ሁለቱ መሪዎች ትኩረት ሰጥተው ከተወያዩባቸው ርዕሶች ዋነኛው የተፈጥሮ ደህንነት ጥበቃ ጉዳይ ነው። ፕረዚደንት ኦባማ በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያን ድርቅ አስመልክተውም ሃሳባቸውን ገልጸዋል። ​​"ከ50 ዓመታት ወዲህ የከፋው ነው የሚባለው ድርቅ በኢትዮጵያ ያስከተለውን የምግብ እጥረት ለመርዳት አስቸኳይ እርምጃ ወስደናል።" - ፕረሲደንት ባራክ ኦባማ

የዩናትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ዛሬ በዋይት ሃውስ ቤተ ማንግሥት በቅቡ አዲስ የተመረጡትን የካናዳ ጠቅላይ ሚንስትር ጁስትቲን ትረዱን ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሁለቱ መሪዎች ትኩረት ሰጥተው ከተወያዩባቸው ርዕሶች ዋነኛው የተፈጥሮ ደህንነት ጥበቃ ጉዳይ ነው።

ከ50 ዓመታት ወዲህ የከፋው ነው የሚባለው ድርቅ በኢትዮጵያ ያስከተለውን የምግብ እጥረት ለመርዳት አስቸኳይ እርምጃ ወስደናል።
ፕረሲደንት ባራክ ኦባማ​

ፕረዚደንት ኦባማ በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያን ድርቅ አስመልክተው የሚከተለውን ብለዋል። "በመጨረሻም በንብጋራቸው መተክላዊ እምነቶች ላይ በማትኮር ለሰብዓዊ ፍጡር እድገትና ለሰው ልጆች ክብር ላለን ቁርጠኛ እምነት እንደ ዓለምአቀፍ ወዳጆች ሥራችንን እንቀጥላለን። በዓለምአቀፍ የጤና ጥበቃ ደህንነት አጀንዳ ተላላፊ በሽታዎች ተዛማች ሆነው ብዙ ሕዝብ ላይ አደጋ እንዳያደርሱ ጥረታችንን እየቀጠልን ነው።" ብለዋል

ፕረዚደንት ኦባማ ለኢትዮጵያ ድርቅ አገራቸው እና ካናዳ እርዳታ እየሰጡ ነው አሉ - ቪድዮ 1
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:16 0:00

"ከ50 ዓመታት ወዲህ የከፋው ነው የሚባለው ድርቅ በኢትዮጵያ ያስከተለውን የምግብ እጥረት ለመርዳት አስቸኳይ እርምጃ ወስደናል። ዛሬ ባለቤቶቻችን ሚሼልና ሦሬ በዓለም ዙርያ ለወጣቶች ትምህርት በተለይም ለሴቶች ልጆች ትምህርትና ጤና የሚያበረክቱትን አስተዋጽዖ ለምቀጠል ቃል ገብተዋል።"

በመቀጠልም፣ "እንዲሁም የእኛ አጋር በመሆን ከሰሃራ በታች ያልይ የአፍሪቃ አገሮች የኤሌትሪክ ኃይል እንዲያገኙ የመጀመርያውን ሥራ የፓዎር አፍሪቃ (Power Africa Initiative) ካናዳ ለመርዳትና የአህጉሪቱን ሕዝብ ከድህነት ለማውጣት እንደምታግዝ ገልጻለች።

የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጉብኝት

ኦባማ ይህንን ንግግር የሰጡት የካናውን ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትረዱን በዋይት ሃውስ በተቀበሉበት ቀን ነው።

ዩናይትድ ስቴትስና ካናዳ የአየር ንብረትን ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ የጋራ ስምምነት ላይ መድረሳተው ተገለጸ።

ይህ ስምምነት ይፋ የሆነው፣ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የካናውን ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትረዱን በተቀበሉበትና ለእንግዳው መሪ ክብር በተካሄደ የእራት ግብዣ ላይ መሆኑ ታውቋል።

ይህ የአሁኑ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ትረዱ የዋይት ሃውስ ጉብኝት፣ ለጥቂት ጊዜ ሻክሮ የቆየውን የዋሽንግተንን እና የአተዋን ግንኙነት ያለሳልሰዋል ተብሎ ይለበቃል።

XS
SM
MD
LG