በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የዒድ መልዕክት


ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማና ቀዳሚት እመቤት ሚሼል ኦባማ
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማና ቀዳሚት እመቤት ሚሼል ኦባማ

የዛሬውን ዒድ አል-ፊጥር አስመልክቶ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የእንኳን አደረሣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡





please wait

No media source currently available

0:00 0:03:48 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የዛሬውን ዒድ አል-ፊጥር አስመልክቶ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የእንኳን አደረሣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ ዳይሬክተር ዴቪድ ኤንሶርም ዒድ ሙባረክ ብለዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማና ቀዳሚት እመቤት ሚሼል ኦባማ
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማና ቀዳሚት እመቤት ሚሼል ኦባማ
ሚሼልና እኔ ዒድ አል-ፊጥርን እያከበራችሁ ላላችሁ በዩናይትድ ስቴትስና በመላው ዓለምም ለምትገኙ ሙስሊሞች የሞቀ ሠላምታችንን እናቀርብላችኋለን - ይላል የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማና የቀዳሚት እመቤቲቱ ሚሼል ኦባማ መልዕክት፡፡

ባለፈው ወር - አሉ ፕሬዚዳንቱ - ሙስሊሞች ዕምነታቸውን በፀሎትና በአገልግሎት፣ በፆምና ከሚወድዷቸው ጋር በመሆን አክብረዋል፡፡ “የዚህ ዓመቱን የዋይት ሃውስ ኢፍጣር ከብዙዎቹ አስተዋፅዖአቸው ዴሞክራሲያችንን ከሚያበለፅገውና ምጣኔኃብታችንን ከሚያጠናክሩት አሜሪካዊያን ሙስሊሞች መካከል ከተወሰኑቱ ጋር በማሣለፌ ክብር ይሰማኛል” ብለዋል ፕሬዚዳንት ኦባማ፡፡

ፕሬዚዳንቱ አክለውም “ብዙዎቻችን ከሙስሊም ጓደኞቻችን እና ባልደረቦቻችን ጋር አብረን ፆሙን ለመፍታት ታድለናል፡፡ ይህ ለተሰጠን በረከት ምሥጋና የምናቀርብበት ሮማዳን ከቤቶቻቸው ተፈናቅለው ከቤተቦቻቸውና ከሚወድዷቸው ተነጣጥለው ያሣለፉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሶሪያዊያንን ጨምሮ ለተከፉ ርሕራሄን ማሣየት እንዳለብን የሚያሳስበን ወግና ልማድ ነው” ብለዋል፡፡

“በዚህ ወቅት ችግር ላይ ለሚገኙት ቁጥራቸው የበዛ ሶሪያዊያን ለዒድ አል-ፊጥር ለመድረስ ዩናይትድ ስቴትስ በምግብና በሌሎችም ሰብዓዊ እርዳታዎች የሚደርስ ተጨማሪ 195 ሚሊየን ደላር መድባለች” ያሉት ሚስተር ኦባማ - ይህም ቀውሱ ከተጫረበት ጊዜ አንስቶ ዩናይትድ ስቴትስ ለሦሪያ ሕዝብ የላከችውን ድጋፍ 1 ቢሊየን ዶላር እንደሚያደርሰው አስታውቀዋል፡፡

“ለብዙ አሜሪካዊያን - አሉ ፕሬዚዳንቱ በራሣቸውና በባለቤታቸው ስም ባወጡት መልዕክታቸው ማብቂያ - ዒድ ኅብሩ ለበዛው የአሜሪካ ልማድና ወግ ታላቅ ጌጥ ነው፡፡ ለሙስሊሞች ሁሉም የተባረከና የደስታ በዓል እንዲሆን እመኛለሁ፡፡ ዒድ ሙባረክ፡፡”በሌላ በኩል ደግሞ የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ ዳይሬክተር ዴቪድ ኤንሶርም የዒድ የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን ሲያሰሙ “እዚህ ቪኦኤ ውስጥ ባሉ ሁሉ ስም ለሙስሊም ተመልካቾቻችንና አድማጮቻችን ሁሉ ዒድ ሙባረክ እላለሁ” ብለዋል፡፡
ዴቪድ ኤንሶር - የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ ዳይሬክተር
ዴቪድ ኤንሶር - የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ ዳይሬክተር
ሚስተር ኤንሶር ቀጥለውም “በሮማዳን ወር ጋዜጠኞቻችን ከዓለም ዙሪያ ዜና እና በተጨማሪም በመላው ዓለም የሚገኙ ሙስሊሞች ይህንን ቅዱስ ወር እንዴት እንደሚያከብሩትና እንደሚያስቡት የሚያሣዩ መረጃዎችን ሲያቀርቡላችሁ ቆይተዋል - ብለው - በዚህ ያለንን የመካፈልና የመታደስ ጊዜም እነዚህ ዘገባዎች ይበልጥ እንደሚያቀራርቡን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ደግሞም የቪኦኤ ዓለምአቀፍ አድማጭና ተመልካች አካል በመሆናችሁም እናመሠግናችኋለን፤ ወሰላም ወ አሌይኩም” - ሲሉ መልዕክታቸውን ደምድመዋል፡፡

ዒድ ሙባረክ
XS
SM
MD
LG