በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሜን ጎንደር በቅማንት ብሔረሰብ አባሎችና በአማሮች መካከል ግጭት በመከሰቱ የበርካታ ሰዎች ህይወት ጠፍቷል


በሰሜን ጎንደር እና አካባቢው በቅማንት ብሔረሰብ አባሎችና በአማሮች መካከል ግጭት መከሰቱና የበርካታ ሰዎች ህይወት መጥፋቱ ትላንት ባስተላለፍነው ዝግጅት ማሰማታችን ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ የችግሩ ሰላባ ከሆኑት መካከል አንድ ሰማቸን ለመግለጽ ያልፈለጉ የትግራይ ተዋላጅን አነጋግረናል።

በጎነደር አከባቢ የግጭት ሰለባ ከሆኑት መካከል አንዱ መተማ ውስጥ ሽንፋዕ በተባለው ቦታ ተጠለው ስለሚገኙት ስዎች ገልጸዋል።

“አሁን ለጊዜው እዚህ ቦታ ላይ ተጠለን ያለነው 400 እንሆናለን። የተቀሩት ደግሞ በሌሎች ገጠሮች ነው ያሉት። ሌላ መጠለያ ሰፈርም አለ። ጥቃት የሚከፍቱብን ሰዎች የከተማይቱ ነዋሪዎች ናቸው። ሆን ብሎ እሚያደራጃቸው ማን እንደሆነ ግን አይታወቅም። ሰው ላይ ደህና ናቸው ንብረት ላይ ግን በሙሉ ነው የዘረፉት። አምሳና ስልሳ የምንሆን የትግራይ ተወላጅ ነጋዴዎች ነበርን። ንብረታችንን በሙሉ ዘርፈውታል። አንድም የቀረ ነገር የለም። እስልካሁን ባለው ጊዜ የተደረገልን እርዳታ የለም። የታሰረ ሰውም የለም። ይህ የጸረ-ሰላም ሰዎች ተግባር በመሆኑ ልትደናገጡ አይገባም። መንግስት የሚያስፈልገውን እርድት ሁሉ ያደርግላችኋል ብለውናል።”

የሀገሪቱ ባለስልጣኖች ቦታው ድረስ ሄደው እንዳነጋገርዋቸውና እንዳጽኗኗቸው የትግራዩ ተወላጅ ገልጸዋል። ያነጋገርዋቸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮን፤ የአመራ ክልል ፕረዚዳንት ደጉ እንዳርጋቸውና አቶ አዲሱ ለገሰ እንደሆኑም ተናግረዋል።

መንግስት የሚያስፈልገውን እርዳታ ሁሉ የዳርግላችኅል። እናንተ ግን ተስፋ ሳትቆርጡ

ለለማት በርትታችሁ ስሩ በማለት ሞራል ሰጥተውናል። እኛም ተቀብለነዋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የኮሙኒኬሽንስ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ስለጉዳዩ ማብራርያ ሰጥተዋል።

“በቅማንቶቻና በአማሮች መካከል ግጭት ተነስቶ ነበር። በመሀሉ የትግራይ ተወላጆችና አገዎች ኢላማ ተደረጉ። የተፈጠረውን ችግር ለማረጋጋት ተብሎ የፌደራልና የክላላዊ መንግስት ባለስልጣኖች ወደ ጎንደርና አከባቢው ሄደው ስለ ወደፊት መፍትሄ ተነጋግረዋል። ባለልጣኖቹ ወደ አከባቢው የሄዱት በቅማንትና በአማሮች መካከል የተፈጠርው ግጭት መፍትሄ እንዲያገኝ ለመጣር ሲሆን ከዛ ጋር በተያያዘ አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች ካሉም ለማየትና መፍትሄ ለማግኘት ነው ወደ አከባቢውም የሄዱት።”

ወደ ጎንደርና አከባቢው የሄዱት የፌደራልና የክልሉ ባለስልጣኖች ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ሊገኝ የሚችልበትን መንገድ ፈልገው እንደተመለሱ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ ጠቁመዋል። ያነጋገራቸው ባልደረባችን በትረ-ስልጣን ነው። አዳነች ፍሰሀየ ታቀርበዋለች።

ሰሜን ጎንደር በቅማንት ብሔረሰብ አባሎችና በአማሮች መካከል ግጭት በመከሰቱ የበርካታ ሰዎች ህይወት ጠፍቷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:02 0:00

XS
SM
MD
LG