በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግብፅ ወደ ናይል ተፋሰስ ትብብር እንደማትመለስ አስታወቀች


የናይል ተፋሰስ ሃገሮች
የናይል ተፋሰስ ሃገሮች
አቶ ዓለማየሁ ተገኑ፤ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር
አቶ ዓለማየሁ ተገኑ፤ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር

please wait

No media source currently available

0:00 0:06:22 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


ግብፅ ወደ ናይል ተፋሰስ ትብብር እንደማትመለስ አስታወቀች፡፡

ግብፅ ይህንን አቋሟን በድጋሚ የገለፀችው ሱዳን ዋና ከተማ ኻርቱም ላይ ትናንት በተካሄደው የትብብር ተቋሙ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ የውኃና የመስኖ ሚኒስትሯ በተወካያቸው ባስተላለፉት መልዕክት መሆኑን የኢትዮጵያ የውኃ፣ የመስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር አለማየሁ ተገኑ ለቪኦኤ በሰጡት ማብራሪያ ገልፀዋል፡፡
የአባይ / ናይል ተፋሰስ
የአባይ / ናይል ተፋሰስ

ግብፅን ጨምሮ አሥር አባላት ያሉትና ኤርትራ በራሷ ፍላጎት በታዛቢነት የሚገኙበት የናይል ወይም የአባይ ተፋሰስ ትብብር ጅማሮ ትናንት ባካሄደው 22ኛው መደበኛ የሚኒስትሮች ስብሰባው ላይ ከግብፅ ጋር ከትብብሩ እራሷን አግልላ የቆየችውንና ባለፈው ዓመት መመለሷን ያሳወቀችውን የሱዳንን የውኃና መስኖ ሚኒስትር ሙታዝ ሙሳ አብደላ ሳሊምን የመጭው ዓመት የትብብሩ ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል፡፡

ተሰናባቿ የደቡብ ሱዳን የውኃና የመስኖ ሚኒስትር ጄማ ኑኑ ኩምባ ግብፅ ወደ ትብብር ተቋሙ ንቁ ተሣታፊ አባልነቷ እንድትመለስ ጠይቀው ለዚህም ከካይሮ ጋር በይፋም ሆነ ይፋ ባልሆኑ መንገዶች ሁሉ መነጋገር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

ግብፅና ሱዳን ዋና ፅ/ቤቱ ኢንቴቤ - ዩጋንዳ ከሚገኘው የናይል ተፋሰስ ትብብር ጅማሮ አባልነት እራሳቸውን ያገለሉት የዛሬ አራት ዓመት /በአውሮፓ አቆጣጠር በ2010 ዓ.ም/ ርዋንዳ፣ ኢትዮጵያ፣ ታንዛኒያና ዩጋንዳ አዲስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ሲፈራረሙ እንደነበረ ይታወሳል፡፡
የናይል ተፋሰስ ሃገሮች
የናይል ተፋሰስ ሃገሮች

ኢትዮጵያም ሆነች ሌሎቹ የትብብር ተቋሙ አባል ሃገሮች ግብፅ እንድትመለስ ጉትጎታቸውን እንደሚቀጥሉ ዛሬ ለቪኦኤ መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያው የውኃ ሚኒስትር አቶ ዓለማየሁ ተገኑ ወደ ትብብሩ መግባት የፍላጎት ጉዳይ ሳይሆን ግድ ነው፤ ሌላ መንገድ የለም ብለዋል፡፡

ግብፅ እአአ በ1929 ዓ.ም እና በ1959 ዓ.ም በወጡ ስምምነቶች ወይም ሠነዶች መሠረት ከ84 ቢሊዮኑ የናይል ውኃ 55 ቢሊዮኑ ይገባኛል የሚል አቋም እንደምታራምድ ይታወቃል፡፡

ከኢትዮጵያ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ከአቶ ዓለማየሁ ተገኑ ጋር የተደረገውን ቃለ-ምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
አባይ
አባይ
XS
SM
MD
LG