በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአባይ ወንዝ የመጠቀም መብትና ዝግጅት


Nile river bank, Egypt
Nile river bank, Egypt

በአባይ ወንዝ ላይ የባለቤትነት መብት ያለው ማነው? በሚለው ጥያቄ ላይ ውዝግቡ እየተባባሰ መሆኑ ይታያል፡፡

የአባይ ምንጭ የሆኑት የበላይ ተፋሰስ ሃገሮች አብዛኛውን መብት ይልቅ ለታችኞቹ እና ተጠቃሚ ለሆኑት ለሱዳንና ለግብፅ የሚሰጡ ስምምነቶችን ጥያቄ ውስጥ አስገብተው እየተፈታተኗቸው ነው፡፡

ኢትዮጵያ በዓለም እጅግ የደኸዩ ከሚባሉ ሃገሮች አንዷ ነች፡፡ አባይ ታዲያ ለረሃቧ መድኅን ይሆን ዘንድ ብዙ ህልም አላት፡፡

በቅርቡ ዐባይ ላይ የተገነባው ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ኢትዮጵያ ያንን ኃይል ለውጭ የመሸጥ ህልሟንም ወደ ዕውንነት ለመለወጥ ሳያግዛት አይቀርም እየተባለ ነው፡፡

ወደመጠናቀቁ እንደተቃረበ የሚነገርለት የመስኖ ፕሮጀክትም ሥር የሰደደውን ረሃብ ለማስወገድና ሰማይ ጠብቆ የሚኖረውንም ገበሬ ድርቁ ባይቀር እንኳ ቢያንስ ከቸነፈር ያተርፈዋል የተባለ ተስፋን እየሰጠ ነው፡፡

ለአባይ ወንዝ 85 ከመቶውን የሚያዋጣው የኢትዮጵያ ምድር እንደሆነ ይነገራል፡፡ በቅኝ አገዛዝ ዘመን የተፈረሙ ሁለት ውሎችን የሙጥኝ ያሉት ሱዳንና ግብፅ ግን ባለመብቶችም፣ አዛዦችም እኛ ነን ባይ ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ የግብፅ አምባሣደር ታሪቅ ኹናይም "የአባይን ውኃ ማግኘት የሕልውና ጉዳይ ነው" ይላሉ፡፡

የአባይ ተፋሰስ የላይኞቹ ወይም የምንጭ ሃገሮች ደግሞ "ግብፅ የማበቃትን ያህን በአባይ ተጠቅማ የአንበሣ ድርሻዋን በተራዘመ ጊዜ አንስታለች፡፡" እያሉ ነው፡፡ ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG