በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ለነገ ረቡዕ ያቀድነው የተቃውሞ ሰልፍ እንደተጠበቀ ነው" የናይጄሪያ የሠራተኞችና ሲቪል ማኅበራት ቡድኖች


የነዳጅ እጥረት በናይጄርያ
የነዳጅ እጥረት በናይጄርያ

ሰልፉ፣ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን በመቃወም የሚካሄድ እንደሆነም ታውቋል።

"ለነገ ረቡዕ ያቀድነው የተቃውሞ ሰልፍ እንደተጠበቀ ነው" ሲሉ፣ የናይጄሪያ የሠራተኞችና ሲቪል ማኅበራት ቡድኖች አስታወቁ።

ሰልፉ፣ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን በመቃወም የሚካሄድ እንደሆነም ታውቋል።

የናይጄሪያ የሠራተኞች ኰንግረስና የዕደ-ጥበባት ኰንግረስ በሰጡት ማስጠንቀቂያ፣ ነዳጅ ዋጋ ከ145 ናይራ ወደ 75 ሳንቲም በጋሎን፣ ከ86.50 ናይራ ወደ 43 ሳንቲም ካልወረደ፣ የተቃውሞ ሰልፉ ላልተወሰነ ጊዜ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

የናይጄርያው ፕረዚደንት ሙሃማዱ ቡሃሪ /ፋይል ፎቶ/
የናይጄርያው ፕረዚደንት ሙሃማዱ ቡሃሪ /ፋይል ፎቶ/

መንግሥት የዋጋ ጭማሬውን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፣ በውጪ ምንዛሪ ሳቢያ የተከሰተውን ቀውስ ለመቀነስ የተደረገ እንደሆነ አመልክቷል። መንግሥት በተጨማሪም፣ ከሠራተኞቹ ማኅበራት ጋር ለመወያየት ቀጠሮ መያዙንም አስታውቋል።

የናይጂሪያ የሠራተኞችና ሲቪል ማኅበራት ጥምረት ዋና ጸሓፊ አቢዮዱን አረሙ እንደተናገሩት ግን፣ ምንም ዓይነት ንግግር ከመጀመሩ አስቀድሞ መንግሥት የነዳጁን ዋጋ ማስተካከል አለበት።

XS
SM
MD
LG