በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ አዲስ የአመጋገብ ለውጥ መመሪያ ወጣ


ሰሞኑን የወጣ የአሜሪካ መንግሥት መመሪያ “እንቁላል ብሉ፤ ቡናም እስከ ስድስት ኩባያ ብትጠጡ የጤና ሥጋት ሊያድርባችሁ አይገባም”ብሏል። ለጤናዎ ያዳምጡት።

የምግብ ማስፈራሪያ እንደአሜሪካዊያን የሚወርድበት የለም ሰዉም በአብዛኛው ጠርጣራና ፈሪ ነው - ወደ አፉ በሚወስደው ላይ። በርግጥ የደፋሩም ቁጥር ጥቂት አይደለም።

የዛሬ አርባ ዓመት አካባቢ /በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር በ1970 ዓ.ም/ የወጣ መመሪያ አሜሪካዊያን ብዙ ቅባት ወደ ሰውነታችን የሚያስገቡ ወይም በሥነ-ምግብ ባለሙያዎቹ አጠራር ኮሌስትሮል የሚያበዙ ምግቦችን ከመመገብ እንዲቆጠቡ በብርቱ ያሳስባል።

ያ መመሪያ ታዲያ በእንቁላልና መሰል በሆኑ እንዲሁም ከእንቁላል በሚሠሩ ምግቦች ምርትና ገበያ ላይ ተፅዕኖ አሳድሮ ቆይቷል።

የምግብ ፒራሚድ
የምግብ ፒራሚድ

ሰሞኑን ከአሜሪካ መንግሥት የሰማነው ግን የተለየ ነው። “እንቁላል ብሉ፤ ቡናም እስከ ስድስት ኩባያ ብትጠጡ የጤና ሥጋት ሊያድርባችሁ አይገባም” ብሏል።

አትብሉ ወይም ባታበዟቸው ይሻላችኋል የተባሉም አሉ፤ ደግሞም አሳምራችሁ ቀርጥፏቸው የተባሉም አሉ።

በዚሁ ዘገባ ውስጥ ስለ ልጅነት ልምሻና ስለኮሌራ ክትባቶች፤ ብዙ መድኃኒቶችን ስለለመደው ዓለምን በጭንቀት ስለዋጠው የትዩበርኩለሲስ - ቲቢ ዓይነት፤ እንዲሁም ሪፐብሊካኖቹ እንደራሴዎቹ “ሽረነዋል” ስላሉት፤ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ደግሞ “መሻሪያችሁን ሽሬዋለሁ” ስላሉበት “ኦባማኬር” የሚል ስም ስለተሰጠው የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የጤና ጥበቃ ዋስትናም የተጠናቀሩ ሪፖርቶችን ያዳምጡ።

የድምፅ ፋይሉ ተያይዟል።

የአሜሪካ አዲስ የአመጋገብ ለውጥ መመሪያ ወጣ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:57 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG