በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተባበሩት መንግሥታት 14ኛው የንግድና ዕድገት ጉባኤ በናይሮቢ ተጀመረ


የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን (ግራ)እና የኬንያ ፕሬዝዴንት ኡሁሩ ኬንያታ (ቀኝ)
የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን (ግራ)እና የኬንያ ፕሬዝዴንት ኡሁሩ ኬንያታ (ቀኝ)

14ኛዉ የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ዕድገት ጉባኤ በናይሮቢ በመካሄድ ላይ ነዉ።ትላንት በተጀመረው ጉባኤ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙንን ጨምሮ የበርካታ አገሮች መሪዎች ተገኝተዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን በጉባኤዉ መክፈቻ ሥነ ሥርአት ላይ ባሰሙት ንግግር ‘ንግድ፥ ቴክኖሎጂንና ኢንቨስትመንትን በትክክልለኛዉ መሪህ ተግባር ላይ ካዋልነዉ ሁሉንም ዜጋ ተጠቃሚ ማድረግ የሚችል ዕድገት ማስመዝገብ እንችላለን’ በማለት ተናግረዋል።

በመክፈቻ ሥነ ሥርአቱ ንግግር ያካሄዱት የኬንያዉ ፕሬዝዴንት ኡሁሩ ኬንያታ ሃገሮች ነጻ የንግድ ቀጠና ሥምምነትን ወደ ተግባር እንዲለዉጡ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።

ለ6 ቀናት የሚቆየዉ የየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንግድና የዕድገት ጉባኤ የዓለም ኢኮኖሚ ዕድገት ቀጣይነት ላይ በማትኮር የተወያየ ሲሆን በተለይ የልማት ፖሊሲ አፈጻጸም አሁን ለተከሰተዉ የዓለም ዕድገት ወደ ኋላ መጓተት ሰበብ ነዉ ሲል ገልጿል።

ጉባኤው በሚቀጥሉት 4 ቀናትም በዝቅተኛ የዕድገት ደረጃ ላይ የሚገኙት ሃገሮች ከዓለም ኢኮኖሚ ተጠቃሚ የሚሆኑባቸዉን አጀንዳ ላይ ይወያያል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የተባበሩት መንግሥታት 14ኛው የንግድና ዕድገት ጉባኤ በናይሮቢ ተጀመረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:56 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG