በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሳልሳ የሙዚቃ ስልት


የታንጎ እና የሳልሳ ዳንስ
የታንጎ እና የሳልሳ ዳንስ

ሳልሳ የሙዚቃ ስልት ስረ መሰረቱ ከኩባና በውሃ ከተከበበችው ደሴት ፖርተሪኮ ነው። የሳልሳ ሙዚቃ ለነዚህ ሁለት ሃገሮች መገለጫቸው የሆነ የባህላዊ የዳንስ ሙዚቃ ነው።

የሳልሳ ሙዚቃ እ.አ.አ በ1970ዎቹ በኒውዮርክ ታዋቂ እየሆነ ተወዳጅነቱም እየጨመረ መጥቶ ነበር። የሳልሳ የሙዚቃ ስልት የተለያዩ የሙዚቃ ስልቶች በውስጡ የያዘ ነው። ሞንቱኖ፣ ጓራቻ፣ ቻቻቻ፣ በጥቂቱ የቦለሮ እንዲሁም የፖርተሪካውያንን ቦምባ እና ፕሌና የሙዚቃ ስልቶች ስብስብ ነው። ላቲን ጃዝ በመባል የሚታወቀው የሙዚቃ ስልትም በሳልሳ የሙዚቃ አቀናባሪዎች፣ በሙዚቃ ተጫዋቾች እንዲሁም የሳልሳ የሙዚቃ መለያ የሆነውና የተወሰኑ ድምፆች ላይ በመመላለስ እንደማጀቢያም እንደምት መጠበቂያም በፒያኖ የሚጫወቱት ዜማ (Piano Guajeo) በኒውዮርክ ሙዚቀኞች በጣም ተወዳጁና በፍጥነትም የሙዚቃ እድገት ያሳየ ስልት ነው።

የኩባው የሳልሳ የሙዚቃ ስልት፤ የስፓኒሽ ዜማ፣ ጊታር እና የአፍሮ-ኩባውያን የምት መሳሪያ ለሰሜናውያኑ አሜሪካውያን ሙዚቃ የጃዝ የሙዚቃ ስልት ቅርብ ነው። ሳልሳ አልፎ አልፎ በሮክ፣ አር ኤንድ ቢ እና በፋንክ የሙዚቃ ስልቶች ውስጥ ይደመጣል።

የሳልሳ ዳንስ ውድድር
የሳልሳ ዳንስ ውድድር

የመጀመሪያዎቹ የሳልሳ የሙዚቃ ባንድ “ኑዮሪካን” የኒውዮርኮቹ የፖርተሪካን ዘሮች ወይም ወደ ነውዮርክ የፈለሱ ፖርተሪካውያን በመባል ይታወቁ ነበር። መገኛው ኩባ የሆነው የሳልሳ ሙዚቃ እና የሙዚቃ ምት ከኒውዮርክ ወደ ኮሎምቢያ እንዲሁም በተቀሩት የአሜሪካ ግዛቶች በፍጥነት ተስፋፍቶ ተወዳጅነቱን እንደጠበቀ በአለም አቀፍ ደረጃ በመደመጥ ላይ ይገኛል። መስታወት አራጋው እና ዲጄ ፋትሱ ያዘጋጁትን አጭር ድምፅ ለመስማት ከበታች ያለውን የድምፅ ምልክት በመጫን ያዳምጡ።

ሳልሳ የሙዚቃ ስልት
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:32 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG