በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሕይወቴ አሥር መርኆች - ሚሚ አለማየሁ


ሚሚ አለማየሁ (የባሕርማዶ የግል ኢንቨስትመንት ኮርፖሬሽን (OPIC) ምክትል ፕሬዝዳንት
ሚሚ አለማየሁ (የባሕርማዶ የግል ኢንቨስትመንት ኮርፖሬሽን (OPIC) ምክትል ፕሬዝዳንት
ሶፊያ አለማየሁ


ትውልድ ኢትዮጵያ አሜሪካዊቷ ሚሚ አለማየሁ ከአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት አንዷ ናቸው፡፡ እአአ በ2010 ዓ.ም ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በእጩነት አቅርበዋቸው በሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ የሙሉ ድምፅ ድጋፍ ከባሕርማዶ የግል ኢንቨስትመንት ኮርፖሬሽን (OPIC) ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ።

ሚሚ በሪፐብሊካኑ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ ተሾመው የአፍሪካ ልማት ባንክ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ተወላጅ አሜሪካዊት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሠርተዋል፡፡ ሚሚ ለአሜሪካ በአፍሪካ ከፍተኛ የገንዘብ ሚኒስቴር ተወካይ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ከአፍሪካ ልማት ባንክ በፊት Trade links የሚባለው የንግድ አማካሪ ድርጅት መሥራች ሆነው አዳዲስ ገበያዎችን ለሚፈጥሩ ደንበኞች በማማከር እና አፍሪካ ውስጥ ንግድን በማስፋፋት ሲሠሩ ቆይተዋል፡፡

ሚሚ አለማየሁን ለመስማት የተገኙ ታዳሚዎች
ሚሚ አለማየሁን ለመስማት የተገኙ ታዳሚዎች

ሚሚ አዲስ አበባ ነው የተወለዱት። ከቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ ኬንያ ሲሄዱ ገና የስምንት አመት ልጅ ነበሩ። ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ሲደርሱ ወደ በካለፎርንያ ተጓዙ።

“ ወቅቱ የአፍሪካ ነው!” የሚሉት ሚሚ ለረጅም አመታት በአፍሪካ እድገት ላይ በተለይም ከአፍሪካ የንግድ ድርጅቶች እና ኩባንያዎች ጋር በቅርበት በመስራት ይታወቃሉ።
ባለፈው ሳምንት ወጣት ኢትዮጵያውያን ባለሞያዎች (Young Ethiopian Professionals,YEP) የተባለው ድርጅት ሚሚን ተጋባዥ እንግዳ አድርዋቸው ነበር ።
“የኜ ታሪክ ከአብዛኛው ስደተኛ ታሪክ ብዙም የተለየ አልነበረም” የሚሉት ሚሚ እንደ አብዛኛው ስደተኛ ሁሉ የባህል መጋጨትን መቐቐም እና እየተማሩ ራስን ለመደገፍ ብዙ ሰአታትን መስራት እንደነበረቸው ያስታውሳሉ።

ሚሚ በእለቱ የህይወት ታሪካቸውን ከመዘርዘር ይልቅ ከልቤ የምመራባቸው እና አሁን ላለሁበት ህይወቴ ምክንያት ናችው የሚሎዋቸውን 10 እሴቶችቻቸውን ለአድማጮቻቸው አካፍለዋል ።

የመጀመሪያው ለውጥ ነው ይላሉ ሚሚ “ተለወጡ፤ ለውጥንም ተቀበሉ- ገና ልጅ እያለሁ ነበር ወላጆቼ ወደ ኬንያ የሄዱት። ይህ ለኔ የመጀመሪያ ፤ትልቅ ለውጥ ነበር። ለመጀመሪያ ግዜ ከአማርኛ ውጪ ሌላ ቁዋንቁዋ ሲነገር የሰማሁት ያኔ ነበር ። ሂደቱ በጣም አሰቃቂ ነው። ለመጀመሪያ ግዜ ከኢትየጵያ ውጪ ሌላ አለም ፤ ሌላ ህዝብ ፤ ቐንቐ ፤ባህል እንዳለ አየሁ። ከዛ ግዜ ጅምሮ በተደጋጋሚ ወደ ተለያየ ቦታ በበጎ ፈቃድ ስሰጥ እና በስራዪ ተጉዜያለሁ፡፡ ለምሳሌ የመጀመሪያ ዲግሪዬን እንዳገኘሁ የስራ ልምምዴን ያደረኩተ በጂኒቫ ነበር። ይህን ያደረኩተ ቐንቐዬን ለማዳበር እና ዩሮፕን ለመጎብኘት ነበር ።ቀጥዬም በቱኒዚያ ሰርቼያለሁ። “
እና እነዚህ ሁሉ ልምዶች ለዛሬ ማንነታቸው መሰረት እነደሆንዋቸው ያናገራሉ ሚሚ አለማየሁ። ልምዶቹ ተዳምረው የተሻልኩ ሰው እንዳደረጋቸው ይናገራሉ።

ስለሁለተኛው የህይወት መመሪያቸው ሲናገሩ “የምትወዱትን ነገር ፈልጉ” ይላሉ ሚሚ፡፡ “ እንደምትገምቱት እንደ ብዙ ኢትዮጵያውያን የኔዎቹም ወላጆች፤ ዶክተር ወይም ኢንጂኔር ብሆን ደስ ባላቸው ነበር። በሳይንስ ጥሩ ነበርኩ፡፡ እና ምናልባትም እነሱ በመረጡልኝ መንገድ ብጘዠ አማካኝ ዶ/ር ወይም ኢንጂነር እሆን ነበር ብዪ አስባለሁ ፤ደስተኛ ግን አልሆንም ነበር። ወላጆቻችን ይህን የሚያረጉት ለኛ በጎ ነገር ስለሚመኙ ነው። የሰው አገር መሆናችንን ያውቃሉ እናም በነዚህ በታወቁ ዘርፎች ብንሰማራ የተሻለ እድል አለን በለው ያምናሉ።”

ሚሚ የልብ ፍላጎትን ስለመከተል ሲያብራሩ ፊልዳቸውን ስቀይሩ እንዳውም የመጀመሪያ ጥቂት ቀናት አባታቸው በጣም እንዳዘኑ እና ለጥቂት ቀናትም እንዳለናገርዋቸው አስታውሰዋል ፡፡ ነገር ግን ያላሉ ሚሚ ሲቀጥሉ “ወላጆቻችን ስለሚወዱን ይቅርታ ያረጉልላን ። እኔ በዛ ግዜ ወላጆቼን ባለመስማቴ በጣም ነው ደስ የሚለኝ፤ የራሴን ምርጫ ባላረግ ኑሮ አሁን ያለሁበት ደረጃ እንደማይደርስም ነበር” ያላሉ፡፡

የሶስተኛው የሚሚ የህይወት መርህ ያለመታከት መማር ነው፡፡ ስለዚሁ ሲያብራሩ “መማር አታቁሙ- ኮሌጅ ብትጨርሱ ፤ ዶክትሬትም እንክዋን ቢኖራችሁ ነገሩ አበቃ ፤ ግባችሁ ላይ ደረሳችሁ ማለት አደለም ። እስከዛሬ ድረስ በተለያዩ ዝግጅቶች ደስ በሚሉኝ ጉዳዮች ላይ የሚናር ሰው ከመጣ ለመስማት እሔዳለሁ፡፡ በተለይ ድግሞ ጉዳዩ የአፍሪካን ፖሊሲ እና እደገትን የተመለከተ ከሆነ። ለምሳሌ ዶ/ር ኦንጎዚ ከናይጀሪያ በጣም ነው የማደቃት። እስዋ ስትናገር መስማት በጣም ነው የሚያስደስተኝ እናም ሁል ግዜ ሳገኛት አንደ ነገር ተምሬ ነው የምወጣው፡፡ እያንዳንዱ ቀን የመማሪያ እድል ነው” ብለዋል፡፡

አራተኛው ይላሉ ሚሚ “አንዳነዴ የምትመኙት ነገር ፈልጋችሁ አጥታችሁት ይሆናል፤ ከኖነም፤ራስችሁ ልትፈጥሩት ሞክሩ- የድህረ ምረቃ ትምህረቴን እነደጨረስኩ በአፍሪካ ንግድ ላይ ያተኮረ ደርጅት ውስጥ መስራት በጣም እመኝ ነበር በወቅቱ አብዛኛው የፈለኩት ስራ ድግሞ የአሜሪካ ዜግነትን ይጠይቅ ነበር ፤ እኔ ደሞ አልነበርኩም፡፡ የፈለኩትን የስራ ልምምድ የሚሰጠነኝ ኩባንያ ፍለጋ ብዙ ግዜዬን በላይብረሪ ውስጥ አጠፋ ነበር።

ሚሚ አለማየሁ (የባሕርማዶ የግል ኢንቨስትመንት ኮርፖሬሽን (OPIC) ምክትል ፕሬዝዳንት) ከወጣት ኢትዮጵያውያን ባለሞያዎች መስራች አባላት ጋር
ሚሚ አለማየሁ (የባሕርማዶ የግል ኢንቨስትመንት ኮርፖሬሽን (OPIC) ምክትል ፕሬዝዳንት) ከወጣት ኢትዮጵያውያን ባለሞያዎች መስራች አባላት ጋር

በመጨረሻ የስራ ማስታወቂያ ባይኖራቸውም፤ ለብዙ ድርጅቶች አብሬአቸው መስራት እንደምፈልግ የሚገልጵ ደብዳቤ ላኩላቸው፡፡ እናም ከንዚህ አንዱ ድርጅት ለስራ ልምምድ ክፍት ቦታ እንደሌላቸው እና ስራ ቢሰጢኝ ምን ላረግ እንደምችል የሚያሳይ የስራ ዝርዝር እንዳቀርብ ነገሩኝ፡፡ የመስራት እድሉ ከተሰተኝ በሀዋላ ግን ስራዬ ስላስደሰታቸው ትምህርት ቤት ስመለስ ከአዲስ ላፕ ቶፕ ጋር በትርፍ ግዜዬ እንድሰራላችው ላኩኝ፡፡” ብለዋል፡፡

ሚሚ ከዚህ ልምዳቸው ተነስተው የሰሩበት ድርጅት የልምምደ ስራ ቃሚ መሆኑን እንደተረዱ ፕሮግራሙን እንደጀመሩ አስታውሰዋል ፡፡ እንግዲህ ያህ የስራ ቦታ ሲጀምር ክፍት አልነበረም፡፡ እንደ ሚሚ አገላለጵ የፈለጉትን መፍጠር መሞከር ማለት እንዲህ ነው ፡፡

የሚሚ አምስተኛ መመሪያ ሁሌም አርያ የሚሆን አስተማሪ /መካሪ
(MENTOR) ማግኘት ነው ፡፡
“ እኔ አስተማሪ /መካሪ የምላቸው ሰዎች አሉኝ። ስራ ሳገኝ ወይ የትብብር ደብዳቤ ስፈልግ ሳይሆን በየግዜው እና በተከታታይ ነው የማገኛቸው ። መቸም ቢሆን ከሌሎች መማር ይቻላል:: አርአያ አስተማሪን በየግዜው ስላረጋችሁት መሻሻሎች፤ የስራ እድገቶች እና የወደፊት እቅዶችን ማሳወቅ አስፈላጊ ነው።” ብለዋል፡፡

በስድስተኛው የሚሚ እሴት ለሌሎች አርአያ /አስተማሪ መሆን ነው። “እኔ በስሬ የምከታተላቸው ሰዎች አሉኝ። ሌሎችን ማስተማር በጣም አስላጊ ሃላፊነት ነው። ጎረቤታቸህ ወይም የወንድችሁ ጓደኛ ሊሆን ይችላል። የሚቀጥለው ትውልድ እናንተን ያያል፤ እናም ከናንተ መማር ይፈልጋል፡፡
ሰባተኛው ይላሉ ሚሚ “ ተዘጋጁ፡ ጠንክራችሁ ስሩ - ምንም ነገር በዋዛ አይመጣም ፤ እኔ ብዙ እንቀልፍ አልባ ቀኖችን አሳልፌያለሁ። አንድን ነገር ለማሳካት መስዋአት መከፈል ያስፋልጋል። በህይወታችሁ በመረጣችሁት ነገር የበላይ ሆናችሁ ለመገኘት ሞክሩ።”

ስምንተኛው እና ለሚሚ ስኬቶች አስተዋጵኦ ካደረጉት እሴቶች መካከል አንዱ ከብልሹ እና ህገ ወጥ ምግባራት መጵዳታቸው መሆኑን ይናገራሉ፡፡ “ስትኖሩ ሌላ ሰው በአጉዪ መነጵር እንደሚያያችሁ ተጠንቅቃችሁ ኑሩ፡፤ ሁለት ግዜ በሹመት ስነ-ስረአት ውስጥ ሳልፍ ደስ ያለኝ ነገር ስርአት እና ህግን የጠበቀ ህይወት መኖሬ ነው። ምን ያህል የግል ሕይወታችሁ ወስጥ ግበተው እንደሚፋትሹ የሚገርም ነው፡፡ በግዜ ግብሬን መክፈሌ፤ የሰሩልኝ ሰዎች ህጋው መኖነቸው በጣም ጠቅሞኛል፡፡” ብለዋል ሚሚ፡፡

በመቀጠልም ሚሚ “ተዝናኑ! ከስራችሁ ደስታን ፈልጉበት፡፡” ብለዋል:: ስለ ዘጠነኛ የህይወት መመሪያቸው ሲያብራሩ “ የዛሬ ሁለት አመት ለገና በአል በዋይት ሀውስ ፓርቲ ላይ ተገኝቼ ነበር። እና ፕሬዝዳንተ ኦባማን “ ክቡር ፕሬዝዳንተ ለአንተ በመስራቴ ትልቅ ክብር ነው የሚሰማኝ” አልኩት። ሚሚ እየተዝናናሽ ጭምር መሆኑን ተስፋ አድጋሉ አለኝ፡፡ መልሱ በጣም ነው የደነቀኝ፤ ትክክለኛ ነው። ብዙ ግዜያችንን በስራ ተጠምደና እናሳልፋለን ግን በስራችን ደስተኞች መሆናችንን መጠየቅ አለብን። ካልሆነም፤ ምናልባት ሌላ ነገር የመፈለጊያ ግዜያችን ነው።” ብለዋል፡፡

የመጨረሻው የሚሚ የህይወት መመሪያ ጥሩ መሆን ነው፡፡ ስለዚህ የህይወት መርሆዋቸው ሲያብራሩ “ጥሩ ሰው ሁኑ! በህየውቴ ብዙ መጥፎ ሰው አጋጥሞኛል። አንዳንደ ሰው አለቃ ስለሆነ ብቻ ክፉ መሆን ያለበት ይመስለዋል ግን ይህ ፍጵሞ ልክ አደለም። ጥሩ ስትሆኑ ሰዎች ለናንተ ሊሰሩላችሁ ፤ሊረድዋችሁ፤ ሊደክሞላቸሁ ፈቃደኛ ናቸው። ከሰዉች የላቀ ነገር የምታገኙት በጎ ስትሆኑ ነው። “ ብለዋል፡፡

ፕሮግራሙ የተዘጋጅው ወጣት ኢትዮጵያውያን ባለሞያዎች (Young Ethiopian Professionals ,YEP) በተባለ በዋሽንግተን ዲስ በተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ በወጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንደ ሚሚ ካሉ ስኬታማ ሰዎች የህይወት ተመኩሮ ፤ ጠንካራ ሰራተኝነት፤ ቁርጠኝነት እና ስኬት ትምህርት እንዲቀስሙ ከማድረግ በተጨማሪ ኢትዮጵያዊያን ባለሞያዎችን በማገናኘት፤ ስራ በማፈላለግ እና አባል ባለሞያዎቹን በአሜሪካ ያሉትን ታዳጊ አትዮጵያዊ ልጆችን በትምህርት እና በምክር እንዲረዱ ፕሮግራሞችን በማዘጀት ይንቀሳቀሳል።

please wait

No media source currently available

0:00 0:09:11 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG