በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

75 ሚልዮን የሚሆኑ አፍሪቃውያን ጉቦ እንደሰጡ አዲስ ዘገባ ገምቷል

የጸረ ሙስና ቡድን ወይም ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል (Transparency International) ባወጣው ዘገባ ባለፈው አመት 75 ሚልዮን የሚሆኑ አፍሪቃውያን ጉቦ እንደሰጡ ይገመታል ይላል። አብዛኞቹ አፍሪቃውያን ሙስና እየተባባሰ ሄዷል እንደሚሉም ዘገባው ጠቁሟል።

የጸረ ሙስና ቡድን ወይም ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል (Transparency International) ባወጣው ዘገባ ባለፈው አመት 75 ሚልዮን የሚሆኑ አፍሪቃውያን ጉቦ እንደሰጡ ይገመታል ይላል። አብዛኞቹ አፍሪቃውያን ሙስና እየተባባሰ ሄዷል እንደሚሉም ዘገባው ጠቁሟል።

ጥናቱን ያካሄዱት ሰዎች ከሰሀራ መለስ ባሉት የአፍሪቃ ሀገሮች ሙስናን በሚመለከት ያላቸውን ተመክሮና እምነት ለማወቅ 43,000 የሚሆኑ ሰዎችን እንዳነጋገሩ ተገልጿል። 58 ከመቶ የሚሆኑት ባለፉት 12 ወራት ውስጥ በሀገሮቻቸው ሙስና እንደተባባሰ ገልጸዋል።

በርካታ የአፍሪቃ ፕረዚዳንቶች ቃል በገቡት መሰረት ሙስና እንዲቀነስ ወይም እንዲጠፋ ዘመቻ ያካሄዱ ቢሆንም ችግሩ በመላ አህጉሪቱ እንደቀጠለ ነው።

ጥናት በተደረገባቸው 18 ሀገሮች ውስጥ ያሉት አብዛኞቹ ሰዎች ሙስናን በመታገል ረገድ በተለይም ፖሊሲንና ፍርድ ቤቶችን በመሳሰሉት አገልግሎቶች መንግስታቱ አልበረቱም ይላሉ። የዜና ዝርዝሩን ከተያይዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

75 ሚልዮን የሚሆኑ አፍሪቃውያን ጉቦ እንደሰጡ አዲስ ዘገባ ገምቷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:09 0:00

XS
SM
MD
LG