በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሚሼል ኦባማ ለሴቶች ትምህርትና እንክብካቤ ቅድሚያ እንዲሰጥ ጠየቁ


Michelle Obama na Cimeira Yali, Washington, Julho 30, 2014
Michelle Obama na Cimeira Yali, Washington, Julho 30, 2014

please wait

No media source currently available

0:00 0:07:52 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የዩናይትድ ስቴትስ ቀዳሚት እመቤት ሚሸል ኦባማ ዋሺንግተን ዲ.ሲ ላይ ለተሰበሰቡ አምስት መቶ የአፍሪካ ወጣቶች ዛሬ ባደረጉት ንግግር ለሴት ልጆች ትምህርትና ደህንነት ትኩረት ሰጥተዋል፡፡

ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች ተመርጠው ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የተጋበዙ 500 ወጣት አፍሪካዊያን መሪዎች፣ ከትናንት በስተያ - ሰኞ፣ ሐምሌ 21/2006 ዓ.ም ከፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ጋር ተገናኝተዋል።

የአፍሪካን የፖለቲካ መሪዎች በሚቀጥለው ሣምንት ለውይይት የጋበዙት ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ “ከአፍሪካ ሀገሮችና ህዝቦች ጋር በእኩልነት ላይ የተመሠረቱ ግንኙነቶችን ማድረግ ተገቢ ነው” ሲሉ ለወጣቶቹ ገልፀዋል።

“ለዚህ የአፍሪካና የዩናይትድ ስቴትስ ግንኙነት ዋልታዎቹ ወጣቶች ናቸው” ብለዋል።

ወጣቶቹ ፕሬዝደንት ኦባማን ከማግኘታቸው በፊት ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪና ከተወካዮች ምክር ቤቱ /ከኮንግረሱ/ አባላትም ጋር ተወያይተዋል።

በትናንት ውይይታቸው ደግሞ የአፍሪካ ወጣቶች በየሃገሮቻቸው ምጣኔ ኃብቶች ላይ ያላቸውን ሚና መክረዋል፡፡

ዛሬ ደግሞ የዩናይትድ ስቴትስ ቀዳሚት እመቤት ሚሸል ኦባማ ንግግር አድርገውላቸዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG