በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕጋዊ ካሏቸው ተቃዋሚዎች ጋር እንደሚደራደሩ ገልጹ


ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ

ህገ መንግስቱንና ህግ መንግስታዊ ስርዓቱን መቀበልና ዓላማቸዉን በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ማራመድን እንደ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠዋል።

የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ዛሬ ለአገር ዉስጥ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ለተለያዩ ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል። በሶማሊ ክልል ከሚንቀሳቀስ ታጣቂ ሃይል ጋር በቅርቡ የተፈረመዉን ስምምነት መነሻ ያደረገዉ ጥያቄ አንዱ ነዉ። መንግስታቸዉ የሚደራደረዉ መሳሪያ ካነሱት ጋር ብቻ ነዉ? ወይስ ካኮረፉትም ጭምር እንደሆነ የተጠየቁት አቶ መለስ፣ “መሳሪያ ለማንሳት ያዉ የመጀመሪያዉ እርምጃ ማኩረፍ ነዉ ስለዚህ ለድርድር ዝግጁ የምንሆነዉ መሳሪያ ቢያነሱም ባያነሱም ካኮረፉት ሁሉ ጋር ነዉ“ ብለዋል። ለምሳሌ አገር ዉስጥ ያሉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በህጉ መሰረት መሥራት የሚፈልጉ እስከሆኑ ድረስ አኩርፈዋል የማይባሉ ስለሆነ መንግስታቸዉ በተከታታይ ድርድር እንዳደረገ ገልጸዉ፣ ያኮረፉና መሰሪያ ያላነሱም ካሉ መንግስት ለመደራደር ዝግጁ ነዉ ብለዋል።

ከተቃዋሚዎች የሚጠበቅ ግን አንደኛ፣ ህገ መንግስቱና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን መቀበልና ማክበር፣ ሁለተኛ የመሰላቸዉን ዓላማ በዚህ ማእቀፍ ዉስጥ በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ማራመድ ነዉ ሲሉ ገልጸዋል።

የሶማሌ ክልል ታጣቂ ድርጅት፣ ከመንግስት ጋር ድርድር ሲያደርግ እነዚህን መስፈርቶች ተቀብሎ ነዉ ሲሉም አክለዋል።

በኡጋንዳ ካምፓላ ዉስጥ የተፈጸመዉን ጥቃት ተከትሎ ተመሳሳይ ሁኔታ በኢትዮጵያ እንዳይከሰት፣ ምን ዝግጅት እንዳለ ተጠይቀዉም ጥንቃቄዉ የተጀመረዉ ከዚያ ቀድም ብሎ እንደሆነ አብራርተዋል።

ለዝርዝሩ የእስክንድፍ ፍሬዉን ዘገባ ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG