በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመድረክ ሊቀመምበር ምእራባውያን መንግሥታት በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብትና ዴሞክራሲ ሁኔታ ላይ ጠንካራ አቋም መያዝ ተስኗቸዋል አሉ


ፋይል ፎቶ - የመድረክ ሊቀመምበር በየነ ጴጥሮስ 
ፋይል ፎቶ - የመድረክ ሊቀመምበር በየነ ጴጥሮስ 

የዮናትድ ስቴትሱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአሁኑ ጉብኝታቸው ከኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ጋር አልተገናኙም፣ ዳሩ ግን፣ ከሁለት ወራት በፊት እንዳነጋገሯቸው ዶ/ር በየነ ገልጠዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ እና ሌሎቹም ምእራባውያን መንግሥታት በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብትና ዴሞክራሲ ሁኔታ ላይ ጠንካራ አቋም መያዝ ተስኗቸዋል ይላሉ የመድረክ ሊቀመምበር በየነ ጴጥሮስ።

የመድረክ መሪዎች መግለጫ እየሰጡ /ፋይል ፎቶ - ሮይተርስ/
የመድረክ መሪዎች መግለጫ እየሰጡ /ፋይል ፎቶ - ሮይተርስ/

የዚህ ምክንኒያቱ የኢህደግ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ ነው የሚሉት ዶ/ር በየነ፣ ይህን አስተያየት የሰጡት የዩናትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአውሮፓ ፓርላማ አባላት ሰሞኑን በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት መነሻ አድርገው ነው። የዮናትድ ስቴትሱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአሁኑ ጉብኝታቸው ከኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ጋር አልተገናኙም፣ ዳሩ ግን፣ ከሁለት ወራት በፊት እንዳነጋገሯቸው ዶ/ር በየነ ገልጠዋል።

እስክንድር ፍሬው ያጠናቀረው ዘገባ አለ ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG