በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የለንደን ርዕሰ-አድባራት ደብረ-ፅዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን


የለንደን ርዕሰ-አድባራት ደብረ-ፅዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን
የለንደን ርዕሰ-አድባራት ደብረ-ፅዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን

የለንደን ርዕሰ-አድባራት ደብረ-ፅዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን ከተመሠረተች አርባ ዓመት ሊሞላ ነው።




please wait

No media source currently available

0:00 0:19:57 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


ከኢትዮጵያ ውጭ፤ በተለይ በእንግሊዝ አገር «ርዕሰ-አድባራት ለንደን ደብረ-ፅዮን ቅድስት ማርያም» በተሰኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስትያን ውስጥ የተነሣውን ውዝግብ ባጭሩ ለመቃኘት ይሞክራል።

የለንደን ርዕሰ-አድባራት ደብረ-ፅዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን ከተመሠረተች አርባ ዓመት ሊሞላ ነው።

ባብዛኛው ዓመታት ቤተክርስትያኒቱ የአገር ቤቱን ሲኖዶስ ትቀበልና፣ ፓትርያርኩን ግን በፀሎት አታነሣም። ይህ ነበር ለዓመታት አካሄዷ።

«ጠንካራ ሕብረት ያላቸውና ለቤተክርስትያንም ቀናዒ የሆኑ አማንያን ያሏት ይህች ቤተክርስትያናችን ዛሬ እንደማይሆን ሆናለች» በማለት ምሬት ያሰሙ አባላት መልዕክት ደረሰን። «በዚህ ታላቅ የፆምና የሱባዔ ወቅት እንኳ መፀለይ አልቻልንም» በማለት የሚያማርሩ ምዕመን በርካታ ናቸው።

እነዚሁ ምዕመናን እንደገለፁት «ቤተክርስትያኒቱ ዛሬ ታሽጋለች። «ማን አሸገው?» ስንል፣ «አስተዳዳሪው አባ ግርማ» ተባልን። አባ ግርማን ጠየቅናቸው። ለውይይቱ «እኔ ባልናገር ይሻላል ስለተባለ፣ ቀሲስ አባተ ያነጋግሩሃል» ተባልኩ። ቀሲስ አባተም ፈቃደኛ ሆኑ፣ ከአቤት ባይ ምዕመናንም አንድ ተወካይ ተሰጠኝ።

አዲሱ አበበ ነው ያዘጋጀው፤ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG