-Fudade Mohammed- ውጤቱን በእርግጥም አደብዝዞታል። ሽብርተኝነቱን አወግዛለሁ።-Feke Burshea- መደብዘዙ ይደብዝዝ። ዋናው አነሱ ሰላም መሆናቸው ነው። ያሸነፈው ልጅ ለሞቱት ቤተሰቦች መፅናናትን በአሜሪካ ሚዲያ ቢመኝ ጥሩ ነው።-Haile Ayele-የሰው ልጅ ሙሉ በሙሉ በጥላቻ ሲሞላ እንዲህ ያለ ያለተገባ ድርጊት ይፈፅማል! ንፁህ ዜጋን እንደወጣ ማስቀረት እንስሳነት ነው!-Yihenew Wagachew-ውጤቱ እንዲያውም ያንፀባርቃል። የአሸባሪዎቹ አላማ ሰላምን ማደፍረስና ትኩረትን መሳብ ነው። ትልቅ መድረክ ስለሆነ። በዚህ ትልቅ መድረክ ማሸነፍ ደግሞ ድሉን አይረሴና አንፀባራቂ ያደርገዋል።-Teshi Tamrat-የማይረሳ ቀን ነው ለነሱ። ድል እና ሃዘን የተቀላቀለበት።-Abdurahman Ibrahim-በቦስተን ማራቶን የተደረገውን የሽብር ጥቃት አወግዛለሁ ግን በዚህ ብቻ አላቆምም! በኢራቅ የተገደሉትን፣ በበርማ፣ በፓለስታይን፣ በካሽሚር፣ በቦዝኒያ፣ በአፍጋኒስታን የሚደረጉትን ጅምላ ጭፍጨፋ በሙሉ አወግዛለሁ!-Sis Hiw-እንደው በሞቴ፥ አሁን ስለውጤት መደብዘዝ መነጋገሪያ ሰዓት ነው? እንኩዋን የጀግኖቻችን ህይወት አልደበዘዘብን፤ የተጎዱትንም ያረጋጋልን ካልን: በሁዋላ ይሄ በሄድንበት እየተከታተለ የንፁሃንን ህይወት የሚቀጥፈውን ፍንዳታ የመጨረሻ ድምፅ የምንሰማው መቼ ነው? ብንል ለስብእናችን የሚመጥን አይመስላችህም? ውድ ቪ.ኦ.ኤዎችም ይሄንን ርዕስ ብታነሱት ወይንም የመነጋግሪያ መንፈሱን ብትቀይሩት ሳይሻል ይቃራል ትላላችሁ?