በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሌሊሣ ዴሲሣ የቦስተን ወርቁን ለከተማው ሊያበረክት ወሰነ


ሌሊሣ ዴሲሣ የቦስተን ማራቶን የወርቅ ሜዳሊያውን ለከተማይቱ እንደሚመልስ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ባሣወቀበት ወቅት
ሌሊሣ ዴሲሣ የቦስተን ማራቶን የወርቅ ሜዳሊያውን ለከተማይቱ እንደሚመልስ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ባሣወቀበት ወቅት

“ስፖርት የጦርነት ሥፍራ አይደለም” - ሌሊሣ ዴሲሣ



ሌሊሣ ዴሲሣ - የቦስተን ማራቶን (2013) አሸናፊ
ሌሊሣ ዴሲሣ - የቦስተን ማራቶን (2013) አሸናፊ

please wait

No media source currently available

0:00 0:05:09 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የ2013 ዓ.ምን (እአአ) ቦስተን ማራቶን ያሸነፈው ኢትዮጵያዊው ሌሊሳ ዴሲሳ የተሸለመውን ሜዳሊያ በዕለቱ ለደረሰው የቦምብ ጥቃት ሰለባዎች ለመስጠት መወሰኑን አስታወቀ።

ለሊሣ ይህንን ውሣኔውን ይፋ ያደረገው አዲስ አበባ ላይ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በተገኙበት ሥነ ሥርዓት ላይ ነው፡፡

ለአፍሪቃ ኅብረት ሃምሣኛ ዓመት በዓል አዲስ አበባ የተገኙት ሚስተር ኬሪ የኢትዮጵያዊውን አትሌት ተግባር አወድሰዋል።

“ስፖርት የጦርነት መድረክ አይደለም” ብሏል ሌሊሣ ለቪኦኤ በሰጠው ቃል፡፡

በቦስተን ማራቶን በወንዶች አንደኛና ሦስተኛ፣ እንዲሁም በሴቶች ሁለተኛ ቦታን የተቆናጠጡት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ለተጨማሪና ዝርዝር መረጃ የያያዘውን የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG