በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያ ተጨማሪ የፓሊስ ሃይል ልታሰልጥን ነዉ


የኬንያ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ ኬንያዉያንን ከጽንፈኞች ጥቃት ለመከላከል ተጨመሪ የፓሊስ ሃይል ያስፈልጋል አሉ።

የኬንያ ፕረዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ 10,000 ተጨማሪ የፖሊስ ኃይል ምልመላ እንዲደረግ ዉሳኔ አሳለፉ።

ፋይል ፎቶ - የኬንያ ፕረዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከናይጄርያ ፕረዚዳንት ቡሃሪ ጋር በሶማልያ በአልሸባባ ለተገደሉ ወታደሮች መታሰብያ በሚደረግበት ወቅት የተነሳ ፎቶ
ፋይል ፎቶ - የኬንያ ፕረዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከናይጄርያ ፕረዚዳንት ቡሃሪ ጋር በሶማልያ በአልሸባባ ለተገደሉ ወታደሮች መታሰብያ በሚደረግበት ወቅት የተነሳ ፎቶ

ፕረዝደንቱ ይህንን የተናገሩት በትላንትናዉ ዕለት ከ1900 በላይ የሚሆኑ አዲስ የፖሊስ አባላትን በኤምባካሲ ባስመረቁበት ወቅት ነዉ።

ኬንያ አብዛኛዉን ጊዜ በተለይም በአሸባሪዉ ቡድን አልሻባብ ጥቃት የሚሰነዘርባት መሆኑን አስታዉሰዉ ፕሬዚደንቱ ዜጎችን ከጽንፈኞች እና ከተለያዩ ወንጀለኞች ለመጠበቅ የሃገሪቱን የፖሊስኃይል ቁጥር ከፍ ለማድረግ የመንግሥታቸዉ ዓላማ መሆኑንንም ይፋ አድርገዋል።

ገልሞ ዳዊት ከናይሮኒ የላከውን ዘገባ፣ ከዚህ በታች ያለውን ፋይል ያድምጡ።

ኬንያ ተጨማሪ የፓሊስ ሃይል ልታሰልጥን ነዉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:38 0:00

XS
SM
MD
LG