በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያዊያን ጠበቆች የባልደረባቸውና ሌሎች ሁለት ሰዎች ሞትን በተመለከተ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ


ኬንያዊያን ጠበቆች የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ
ኬንያዊያን ጠበቆች የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ

የሥራ ባልደረባቸውና የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቹ ዊሊ ኪማኒ፣ የደንበኛው ጆስፓት መወንዳ እንዲሁም የሹፌራቸውን ሞት ያስቆጣቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ የኬንያ የሕግ ባለሞያዎች ዛሬ በናይሮቢ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ። ሕገ-ወጥ ግድያን አስመልክቶ በዚህ ሳምንት የተካሄደ ሁለተኛው ትልቁ የተቃውሞ ሰልፍ መሆኑም ታውቋል።

በመቶዎች የሚቆጠሩ የሕግ ባለሞያዎች ወይንጠጅ ሪቫን በማሰር ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ፖሊስ ኢንስፔክተር ጽ/ቤት ማምረታቸውን ታውቋል።

ኬንያዊያን ጠበቆች የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ
ኬንያዊያን ጠበቆች የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ

ጠበቃዎቹ የሥራ ባልደረባቸው ዊሊ ኪማኒ ፣ ደንበኛቸው ጆስፓት መወንዳ እና ሹፌራቸው ጆሴፍ ሙሪሪ በሕገ-ወጥ መንገድ መገደሉን በመቃወም የተቃውሞ ሰልፉን ያካሄዱ ሲሆን የሞቱት ግለሰቦች አስክሬን ከናይሮቢ 70 ኪሜ ርቀት ላይ በሚገኝ ወንዝ ውስጥ ተጥሎ መገኘቱንም ታውቋል።

ቻርለስ ካንጃማ በኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከራካሪ ጠበቃና በኬንያ የማኅበረሰብ ሕግ ተቋም ሰብሳቢ ናቸው። “ተቃውሞውን ያካሄድነው ግንዛቤ ለመፍጠር ነው። የሕግ ባለሞያዎች ላይ ጥቃት መፈጸም እንደማይቻል ለመግለጽም ነው። ምክንያቱ የሕግ ባለሞያዎች ላይ ጥቃት ማድረስ በሕዝብና በሀገር ላይ ጥቃት የማድረስ ያህል ነው። ይህ ማለት ደግሞ ማንኛው ሰው በአስተማማኝ ሁኔታ ውስጥ አይደለም” ይላሉ።

ሦስቱ ሰዎች ደብዛቸው የጠፋው ከሰኔ 23 ችሎት በኋላ ነበር። ከሳምንት በፊት ጠበቃ ዊሊ ኪማኒ የፖሊስ እጅ አለበት የተባለዉን የደንበኛቸው ሜወንዳ በትራፊክ ፖሊስ በስሕተት በጥይት እጁን መቁሰሉን በመቃወም በክርክር ላይ ነበር። ነገር ግን ባልታወቀ ሁኔታ ከታክሲ ሾፌራቸው ጋር ተገድሎ በጆንያ ተጥሎ ተገኝቷል። የደምበኛው ሕይወትም አልፏል።በተደረገው አስክሬን ምርመራም ሟቾች ክፉኛ መደብደባቸው ታውቋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

ኬንያዊያን ጠበቆች የባልደረባቸውና ሌሎች ሁለት ሰዎች ሞትን በተመለከተ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:02 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG