በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያ የአልሸባብ ታጣቂዎች አንድ የአካባቢ ባለሥልጣን ተኩሰው ገደሉ


ሰሜን ምሥራቅ ኬንያ ውስጥ ተጠርጣሪ የሶማሊያው “ፅንፈኛ ቡድን” የአልሸባብ ታጣቂዎች አንድ የአካባቢ ባለሥልጣን ተኩሰው ገደሉ።

ሰሜን ምሥራቅ ኬንያ ውስጥ ተጠርጣሪ የሶማሊያው “ፅንፈኛ ቡድን” የአልሸባብ ታጣቂዎች አንድ የአካባቢ ባለሥልጣን ተኩሰው ገደሉ።

ጥቃቱ ትናንት ሰኞ ማታ የደረሰው ኦማር ጂሎ በምትባለው ከማንዴራ ከተማ ሃያ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ መሆኑን ባለሥልጣናቱ ገልፀዋል።

ታጣቂዎቹ ሁለት የኬንያ ፖሊሶችን አግተዋል የተባለውን ግን የማንዴራ አውራጃው ባለሥልጣን አስተባብለዋል።

የአልሻባብ ታጣቂዎች ሰሜን ኬንያ ውስጥ በአምሥት ቀናት ውስጥ ያደረሱት ሁለተኛ ጥቃት መሆኑ ነው።

ባለፈው ሣምንት ሃሙስ ማታም ኤልዋክ ከተማ አጠገብ ጥቃት አድርሰው ሁለት ሰዎች ገድለዋል።

ማንዴራ እስከመጪው ሰኔ ወር መጨረሻ ድረስ የሚዘልቅ የሰዓት ዕላፊ ታውጁዋል። ባለፈው ጥቅምት የሰዓት እላፊው የታወጀው አውራጃዋን የአልሸባብ ጥቃት ከደጋገማት በኋላ ነው።

ይህ በዚህ እንዳለ ሶማሊያ ውስጥ ከባይዶዋ ከተማ ዘጠና ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለችው ካንሳሂዴሬ ከተማ ሻይ ቤት ውስጥ በደረሰ ፍንዳታ ሰባት ሰዎች ቆስለዋል። ሁለቱ የከተማዋ ባለልሥጣናት ናቸው፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG