በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጆብስ ታስቦ ዋለ

ከካሊፎርኒያ የአፕል ሱቆች በአንዱ የስቲቭ ጆብስ አፍቃሪዎች ያኖሯቸውን ማስታወሻዎች ማምሻውን ሠራተኞቹ ሰብስበዋል፡፡ በዓለም ዙሪያ በርካታ የአፕል መደብሮች ጥቅምት ስምንት ቀን መሥራቻቸውንና ዋና ሥራ አስፈፃሚያቸውን ስቲቭ ጆብስን ለመዘከር ዝግ ሆነው ውለዋል፡፡
ከካሊፎርኒያ የአፕል ሱቆች በአንዱ የስቲቭ ጆብስ አፍቃሪዎች ያኖሯቸውን ማስታወሻዎች ማምሻውን ሠራተኞቹ ሰብስበዋል፡፡ በዓለም ዙሪያ በርካታ የአፕል መደብሮች ጥቅምት ስምንት ቀን መሥራቻቸውንና ዋና ሥራ አስፈፃሚያቸውን ስቲቭ ጆብስን ለመዘከር ዝግ ሆነው ውለዋል፡፡

ረቡዕ ጥቅምት 8 ቀን የስቲቭ ጆብስ መታሰቢያ ቀን ነበር፡፡

ስሙ በዓለም የገነነውና የዘመናችን የፈጠራ ሰው ተብሎ የተጠራው ቴክኖሎጂስት ስቲቭ ጆብስ ሥራዎችና ድንቅ ውጤቶች አንዷ የሆነችው "አይፎን ፎር ኤስ" በይፋ ሥራ በጀመረችበት በትናንትናው ዕለት በመላው ዓለም ያሉ የስቲቭ ጆብስ ወዳጆች፣ አድናቂዎችና የአፕል ኩባንያ ሠራተኞች ዘክረውት ውለዋል፡፡

ከመገናኛ እስከ መዝናኛ የአፕል ውጤቶች ዓለማችን መረጃ የምታገኝበትን፣ የምትለዋወጥበትንና ቴክኖሎጂን የምትጠቀምበትን ሥርዓት፣ አያያዝና አመራር ፍፁም ባልነበረና በአዲስ መስክ ላይ አስቀምጠውታል፡፡

"አፕል እነዚያን የተቀቁ መሣሪያዎች ስለቴክኖሎጂ ብዙም ግድ የሌላቸው ሰዎች እንኳ ቀላልና ያለችግር የሚገቡ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል" ብለዋል በደቡብ ካሊፎርኒያው የአነንበርግ የኮምዩኔኬሽ እና ጋዜጠኝነት ኮሌጅ ባልደረባው አንድሩ ሊህ፡፡

አፕል ዛሬ ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ካፒታል ያለውና በመላው ዓለም ከአራት ሺህ በላይ ሠራተኞች ያሉት ግዙፍ ኩባንያ ነው፡፡

ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG