በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም አቀፉ ፍልሰት ድርጅት ታንዛኒያ 74 የኢትዮጵያ ፍልሰተኞች ወደ ሃገራቸዉ የሚመለሱበትን መንገድ እንዲያመቻች ጠየቀ


ታንዛኒያ 74 የኢትዮጵያ ፍልሰተኞች ወደ ሃገራቸዉ የሚመለሱበትን መንገድ እንዲያመቻች የዓለም አቀፉ ፍልሰት ድርጅት (IOM) ጠየቀ። ፍለሰተኞቹ በታንዛኒያ ዉስጥ በህገ-ወጥ መንገድ በመግባት ተይዘዉ የእሥር ጊዜያቸዉን ከጨረሱ በኋላ ከሶስት ሳምንት በፊት ወደ ኬንያ ድምበር ሊሻገሩ የነበሩ ናቸዉ። የኬንያ መንግስት በጊዜዉ ፍልሰተኞቹ መመለስ ያለባቸዉ ወደ ትዉልድ ሃገራቸዉ ኢትዮጵያ እንጂ ወደ ኬንያ አይደለም ሲል ኢትዮጵያዉያኑ ወደ ድምበሩ እንዳይገቡ ፍቃድ ከልክሏቸዋል።

የታንዛኒያ ኢሚግሬሽን ጉዳይ በኪሊማንጃሮ ግዛት በቁጥጥር ስር የሚገኙ 74 የኢትዮጵያ ፍልሰተኞች ወደ ሃገራቸዉ የሚመለሱበትን መንገድ እንዲያመቻች የዓለም አቀፉ ፍልሰት ድርጅት (IOM )ጥሪ አቅርቧል።

ፍልሰተኞቹ በታንዛኒያ ዉስጥ በህገ-ወጥ ዝዉዉር ታስረዉ የእስር ጊዜያቸዉን የጨረሱ ሲሆኑ፤ የታንዛኒያ መንግስት ከ3 ሳምንታት በፊት በኬንያ ድምበር በኩል ወደ ሃገራቸዉ እንዲመለሱ ለማድረግ ቢሞክርም የኬንያ የድመበር ጠባቂዎች ኢትዮጵያዉያኑን ወደ ኬንያ ድምበር እንዳይገቡ ከልክሏቸዋል።

ፍልሰተኞቹ ወደ ኬንያ እንዲሻገሩ ታቅዶ የነበረዉ በኬንያ - ታንዛኒያ ድምበር በምትገኘዉ ታቬታ ግዛት ነበር። በግዛቱ አንድ የመንግስት ኃላፊ፣ "እነዚህ ኢትዮጵያዉያን መመለስ ያለባቸዉ ወደ ሃገራቸዉ ኢትዮጵያ እንጂ ወደ ኬንያ አይደለም። የታንዛኒያ መንግስት ያንን ማድረግ ሲገባዉ ወደ ኬንያ መንግስት ፍልሰተኞቹን መጣሉ ተገቢ አልነበረም" ሲሉ ለአሜርካ ድምጽ ተናግረዋል።

በታንዛኒያ የኪሊማንጃሮ ክልል የኢሚግሬሽን ኃላፊ የሆኑት ማንኩጉ እንዳሉት ኢትዮጵያዉያኑ ወደ ሃገራቸዉ ለመለስ የታንዛኒያ መንግስት በቂ ባጀት ስለሌለዉ በታንዛንያ ዋና ከተማ ዳረ ሰላም የሚገኘዉ ዋና ቢሮዋችን የዓለም አቀፉ ፍልሰት ድርጅትን (IOM) እርዳታ ጠይቀዋል በማለት ለአሜርካ ድምጽ ተናግረዋል።

የፍልሰተኞቹ ጉዳይ የሚመለከተዉ በኬንያ ናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በበኩሉ ስለፍልሰተኞች ሰምቻለሁ በእርግጥ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን በማጣራት ላይ ነን ብለዋል፣ አቶ አንዳርጉ በርሄ በኬንያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ሁለተኛ ጸሃፊ።

አክለውም፣ መረጃዉ አለን ከሞሽ ኪሊማንጃሮ አካባቢ ለነበሩት 74 ልጆች እሥራቸዉን ጨርሰዉ ወደ ኬንያ ድንበር ነዉ ዲፖርት ያደረጓቸዉ ብለዋል።

የታንዛኒያ መንግስት አሁን ምንድነዉ ግን እዝያ ችግር የነበረዉ፣ ሰዎቹ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን የሚገልጽ ሰነድ የላቸዉም፣ ሰነድ ስለሌላቸዉ እነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያዉያን ናቸዉ አይደሉም የሚል ነገርም ስለ ነበረዉ፣ ሌሴፓሴ መያዝ አለበት አንድ ሰዉ ኤምባሲዉ መነገር አለበት፣ ስለዚህ ጉዳዩን እየተከታተልነዉ ነዉ አሁን ሞሽ ነዉ የሚገኙት ልጆቹ እኛጋ ፕሮሰስ ለማድረግ ደብዳቤ እንጽፋለን ሊስታቸዉን እንልካለን ብለዉ ነበረ፣ እሱን በመጠባበቅ ላይ ነዉ ያለነዉ ይላሉ አቶ አንዳርጉ በርሄ።

እንዴት ነዉ የምትለይዋቸዉ? ብለን ላቀረብንላቸው ጥያቄም፣

"ኢትዮጵያዊ ነህ አይደለህም እንደ መንግስት የምናደርገዉ የራሳችን አሰራር አለን። ይሄ የኤምባሲዉና የመንግስት ሥራ ነዉ። ወደዝያ ሄደን ነዉ የሚናጣራዉ። አሁን ከእነሱ ጋር ተነጋግረናል በስልክም ተደዋዉለናል። ኦፊሴላዊ የሆነ ደብዳቤ እና ሊስታቸዉን ላኩልን ባስቸኳይ ብለናቸዋል። እነሱም እንልካለን ብለዋል። እንግዲህ ያዉ በእነሱ አንዳንድ ነገር እየጣሩ ይሆናል የሚልኩት ከዚያም በአስቸኳይ እኛ ለመንግስታችን እናሳዉቃለን። መንግስት በሚሰጠን አቅጣጫ መሰረት ከዝያ ጉዳዩን እንፈጽማለን።" ብለዋል አቶ አንዳርጉ በርሄ።

የነገሩን ቅድመ ሁኔታ ምን ያክል ጊዜ ይፈጃል? ብለን ላቀረብንላቸው ጥያቄ፣ እንግዲህ እኛ በመጣልን ሰዓት ነዉ እርምጃ የምንወስደው ብለዋል።

ዓለምአቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት አርማ
ዓለምአቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት አርማ

የኢትዮጵያዊኑን ሁኔታ በማስመልከት ታንዛንያ ወደ የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM)አቤቱታ አቅርባለች፤ ነገር ግን እስካሁን የተሰጠ መግለጫ የለም።

ጉዳዩን ከናይሮቢ ለአሜርካ ድምጽ ገልሞ ዳዊት ተከታትሎ አጠናቅሮታል፣ ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG