በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፀረ ትኋን መድኃኒት በኢትዮጵያ


ተመራማሪ ንጉስ ገብረ መድህን
ተመራማሪ ንጉስ ገብረ መድህን

የመድኃኒት ቅመማ እና የሕብረተሰብ ጤና ሳይንስ ባለሞያ አቶ ንጉስ ከሦስት ንጥረ ነገሮች ቀምመው ያዘጋጁት ይህ መድኃኒት በአንድ የገጠር መንደር ውስጥ ተሞክሮ ውጤታማ መሆኑን ተረጋግጧል።

አቶ ንጉስ ገብረመድህን የተባሉ ኢትዮጵያዊ የሰው ልጅና እንስሳትን የመጉዳት መርዛማ ይዘት የሌለው የትኋን መድኃኒት ቀምመው አዘጓጅተዋል።

የመድኃኒት ቅመማ እና የሕብረተሰብ ጤና ሳይንስ ባለሞያ አቶ ንጉስ ከሦስት ንጥረ ነገሮች ቀምመው ያዘጋጁት ይኸው መድኃኒት በአንድ የገጠር መንደር ውስጥ ተሞክሮ ውጤታማ መሆኑን ተረጋግጧል።

አንዱ መድኃኒቱን ለመቀመም የተጠቀሙበት ንጥረ ነገር ሜንታ ከረሜላ ነው። ሰዎች ከረሜላውን ስለሚበሉት በፍጹም ጉዳት የሌለው በመሆኑ መድኃኒቱ በዲዮደራንትና ኤር ፍሬሽነር መልክ ለህጻናት ጭምር ቢሰጥ ስለሚችል ተመራጭ ያደርገዋል ብለዋል ተመራማሪው።

ተመራማሪ ንጉስ ገብረመድህን
ተመራማሪ ንጉስ ገብረመድህን

ከአሁን በፊት ጥቅም ላይ ይውሉ የነበሩት እንደ ማታይንና ዲዲቲ የመሳሰሉት የመርዝነት ባህሪ ያለባቸው መድኃኒቶች በሰው እና በእንስሳት ከፍተኛ ጉዳት ከማድረሳቸውም በላይ ትኋንን የመግደል አቅማቸው መቀነሱን ሌላ መድኃኒት ለመቀመም ዓለማዊ ሁኔታው ያስገድዳል ይላሉ አቶ ንጉስ።

በዓለምአቀፍ ደረጃ የታገዱ ጎጂ ኬሚካሎች ዲዲቲ፣ ፒሲቢ እና ዲዮክሲን ይገኙበታል
በዓለምአቀፍ ደረጃ የታገዱ ጎጂ ኬሚካሎች ዲዲቲ፣ ፒሲቢ እና ዲዮክሲን ይገኙበታል

የኢትዮጵያ የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን መድኃኒቱ መርዛማ ባህሪ እንደሌለውና ጥቅም ላይ መዋል እንዳለበት ማረጋገጫ ሰጥቷል።

ከአቶ ንጉስ ጋር በምርምሩ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትም መሳተፋቸው ተገልጿል። እነሱም ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ ዶክተር መኮንን፣ ዶክተር ኪዳነ፣ ዶክተር ወንድወሰን እና ረዳት ፕሮፌሰር ዳግማዊ ዓሊ ናቸው። ሙሉውን ዘገባ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

የፀረ ትኋን መድኃኒት በኢትዮጵያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:31 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG