በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አይኤልኦ ኢትዮጵያን ለሠራተኞች መብቶች "ክፉ" ሃገር ሲል ፈረጀ


የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የሥራ ድርጅት - አይኤልኦ
የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የሥራ ድርጅት - አይኤልኦ

የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የሥራ ድርጅት - አይኤልኦ ኢትዮጵያን የሠራተኞችን መብቶች በማክበር በኩል የከፋች ሃገር ናት ሲል በቅርቡ ሪፖርት አውጥቷል፡፡




የአይኤልኦ አካል የሆነው የደራጀት ነፃነት ኮሚቴ ወደ 55 ዓመታት ለሚሆን ጊዜ በሥራ ላይ ያለ ተቋም ነው፡፡

ዛሬ 186 ሃገሮች የሥራ ድርጅቱ አባላት ሲሆኑ ዋና ዋና የሚባሉ ስምምነቶቹንና ሠነዶቹን በየሃገሮቻቸው የሕግ አውጭ አካላት አስፀድቀው ፈርመዋል፡፡

ከእነዚህ ዋና ዋና እና ቁልፍ ከሚባሉ ስምምነቶች መካከል በማኅበር የመደራጀት ነፃነት ስምምነት፣ ለመደራጀት መብት የሚሰጥ ጥበቃ ስምምነት፣ የወል ድርድር መብት ስምምነት የሚጠቀሱ ሲሆን ኢትዮጵያም እነዚህንና ሌሎቹንም ስምምነቶች ተቀብላ ፈርማቸዋለች፡፡
ፕሮፌሰር ፖል ፋን ደር ሃይደን - የአይኤልኦ የመደራጀት ነፃነት ኮሚቴ ሊቀመንበር
ፕሮፌሰር ፖል ፋን ደር ሃይደን - የአይኤልኦ የመደራጀት ነፃነት ኮሚቴ ሊቀመንበር

በመሆኑም ኢትዮጵያ ስምምነቶቹን የማክበር ግዴታ እንደሚጠበቅባት የአይኤልኦ የመደራጀት ነፃነት ኮሚቴው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ፖል ፋን ደር ሃይደን ገልፀዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የሥራ ድርጅት - አይኤልኦ ኢትዮጵያን የሠራተኛ መብት የማያከብሩ ክፉ ሃገሮች ዝርዝር ውስጥ ያሠፈረበት ድምዳሜ ላይ የደረሱት ኮሚቴአቸው የእነዚያን ስምምነቶች መጣስን የሚመለከቱ ስሞታዎችን የሚመረምር በመሆኑና እንዲህ ዓይነት አቤቱታዎችም ከኢትዮጵያ የደረሱት በመሆኑ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ዘገባውን ያዳምጡ፡፡
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:57 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG