በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢጋድ የደቡብ ሱዳንን ጉዳይ ማብራሪያ ይዞ ወደ ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሄደ


አምባሣደር ስዩም መስፍን
አምባሣደር ስዩም መስፍን

በደቡብ ሱዳን ዋና አደራዳሪ አቶ ስዩም መስፍን የተመራ የምሥራቅ አፍሪካ ሃገሮች የጋራ ልማት ባለሥልጣን - ኢጋድ ልዑካን ቡድን ወደ ወደ ዓለሙ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ሄዷል፡፡

ቡድኑ ከአዲስ አበባ ወደ ኒው ዮርክ የተነሣው ትናንት ሲሆን አባላቱ ሰሞኑን ከፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ ጋር ሲገናኙ የደቡብ ሱዳን ባላንጦችን ለማገናኘት እና ለማወያየት ሲያደርግ በቆየው ጥረት ላይ ማብራሪያ ለመስጠንና ለመወያየት መሆኑን ለባለሥልጣኑ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልፀዋል፡፡

ኢጋድ የያዘው ሽምግልና አካል የሆነው ብዙ ወገኖችን ያሳትፋል ተብሎ ተጠብቆ የነበረው የአዲስ አበባ ድርድር የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይቱ ውክልና ጉዳይ አላስደሰተንም በሚል ተቃዋሚዎቹ ተደራዳሪዎች ለከትናንት በስተያ ሰኞ ተይዞ በነበረው የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ሳይገኙ መቅረታቸው ይታወሳል፡፡

የውይይቱን መስተጓጎል አስመልክቶ በተቃዋሚዎቹ ላይ የተሰማውን ቅሬታ ኢጋድ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

የኢጋዱ ቡድን በኒው ዮርክ ጉዞው በማንኛውም ወገን ላይ እንዲወሰድ የሚፈለግን እርምጃ አስመልክቶ የያዘው በግልፅ የተነገረ ሃሣብም ሆነ ጥያቄ አለመኖሩን ምንጮቹ አክለው አመልክተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG