በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ከ1ሺህ 6መቶ በላይ ሰዎች ታስረዋል


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

በኢትዮጵያ ካለፈው መስከረም 28 ጀመሮ ሥራ ላይ እንዲውል የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ትኩረት በመንግሥቱ ላይ ተቃውሞ ያላቸውና ትችት የሚያቀርቡትን ለማፈን ነው የሚሉ ሀገሪቱ ውስጥ የሚወጡ ዘገባዎች እየጠቆሙ ነው፡፡

የዐዋጁ ሀሳብ

“ተቃዋሚዎች ሳይሆኑ አይቀሩም” የሚባሉ ተጠርጣሪዎችንም መሆኑንም ዘገባዎች ይናገራሉ፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት

“ወሮበሎች” ወይም “ቀንደኛ መሪዎች” ያላቸውን ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎችን ማሠሩን ከገዠው ፓርቲ ጋር ቁርኝት እንዳለው የሚነገረው የዜና አውታር ፋና ብሮድካስቲንግ ኮረፖሬት ዘግቧል፡፡

በፋና ዘገባ መሠረት የታሠሩት ሰዎች ቁጥር አንድ ሺህ 175 ይላል፡፡

በአማራ ክልል 93 ኢትዮጵያውያን የታሠሩበት ሰሜን ጎንደር፣ በኦሮምያ ክልል ውስጥ የሚገኙት 110 ኢትዮጵያዊያን የታሠሩበት ቄለም ወረዳ፣ 302 ኢትዮጵያዊያን የታሠሩበት ጉጂ፣ 670 ኢትዮጵያዊያን የታሠሩበት ምዕራባዊ አርሲ፣ ከፍተኛ ተቃውሞ የሚካሄድባቸው አካባቢዎች መሆናቸው ይታወቃል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ሂዩማን ራይትስ ዋች ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ መሠረት ቢያንስ 1ሺህ 600 ሰው ማሠራቸውን አስታውቀዋል፡፡

“ዐዋጁ ተቃውሞ ከተጀመረበት ከአንድ ዓመት በፊት አንስቶ መንግሥት ሲያካሂድ የነበረውን ተግባር በይፋ የተፈቀደ ሳያደርገው አልቀረም” ብሏል ሂዩማን ራይትስ ዋች አክሎ፡፡

የኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ
የኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ፡፡

በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ከ1ሺህ 6መቶ በላይ ሰዎች ታስረዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:44 0:00

XS
SM
MD
LG