በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሥጋ ጥሬውን አትብሉ...


ሥጋ ጥሬውን አትብሉ
ሥጋ ጥሬውን አትብሉ

... እና ሌሎችም የጤና ጉዳዮች ዘገባዎች




አፍሪካና ኤድስ
አፍሪካና ኤድስ


በ2012 ዓ.ም በዓለም ዙሪያ በኤችአይቪ የተያዘ አዲስ ተጋላጭ ቁጥር ‘2.3 ሚሊየን ብቻ ነው’ ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ መርኃግብር - ዩኤንኤድስ አስታውቋል፡፡
በሕፃናት ዘንድ ይደርስ የነበረው በአዲስ ሁኔታ የመጋለጥ መጠን በ52 ከመቶ አሽቆልቁሏል፡፡
እአአ በ2015 ዓ.ም ማንም ሕፃን ኤችአይቪን ይዞ እንዳይወለድ ወይም ሲወለድ ለኤችአይቪ እንዳይጋለጥ ለማድረግና ከኤድስ ነፃ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል የተባለ “ዘመቻ ዜሮ” በዓለም ዙሪያ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ከዓለም የኤችአይቪ ተጋላጭነት እና ኤችአይቪ በደሙ ውስጥ ከሚገኘው ሰው ብዛት ሰባ አምስት ከመቶው የሚገኘው አፍሪካ ውስጥ ነው፡፡
*********


ዓለምአቀፍ የቀይመስቀል ኮሚቴ /አይሲአርሲ/
ዓለምአቀፍ የቀይመስቀል ኮሚቴ /አይሲአርሲ/


ዓለምአቀፉ የቀይመስቀል ኮሚቴ በአንዳንድ የአፍሪካ፣ የእሥያና የደቡብ አሜሪካ አካባቢዎች ለሚያካሂዳቸው ፈጥኖ ደራሽ ተግባራት የበጀት እጥረት እያጋጠመው ነው፡፡

ጠቅላይ ፅሕፈት ቤቱ ጄኔቫ የሚገኘው ዓለምአቀፉ የቀይመስቀል ኮሚቴ /አይሲአርሲ/ በሰማንያ ሃገሮች ውስጥ በ1.21 ቢሊየን ዶላር የሚያካሂዳቸው የነፍስ ደራሽ ሥራዎች ያሉት ሲሆን አሁን በእጁ የሚገኘው ከሚያስፈልገው ግማሹ ብቻ መሆኑን አስታውቋል፡፡
**********


ሥጋ ጥሬውን አትብሉ
ሥጋ ጥሬውን አትብሉ

ጥሬ ሥጋ የሚያስከትላቸው የጤና ችግሮች የበዙ በመሆናቸው ሰዉ ሥጋ ጥሬውን እንዳይበላ የጤና ባለሙያዎች አጥብቀው እየመከሩ ነው፡፡

በግልፅ ከሚታዩት ኮሦና የመሳሰሉ ተላላፊ ተውሣኮች ሌላ እንደልብ ሕመም፣ ከባድ የደም ግፊት እና ሌሎችም ውስብስብ የጤና ችግሮች እንደሚያጋልጥ ባለሙያዎቹ ይናገራሉ፡፡

የማርቴ ፋን ደር ቮልፍን በቪድዮ የተደገፈ ዘገባ ለማየት ይህንን ማገናኛ ይጫኑና ይከተሉ፡፡
http://www.voanews.com/content/health-risks-fail-to-deter-ethiopians-from-eating-raw-meat/1753640.html


ለሙሉው ዘገባ ከዚህ በታች ያለውን ማጫወቻ ከፍተው የድምፅ ፋይሉን ያዳምጡ፡፡
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:33 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG