በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞው የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው የእስር ቤት ታሪኮች


የቀድሞው የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው
የቀድሞው የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው

"አንድ እስረኛ ተመርምሮ ሲመለስ መጀመሪያ የሚቀርብለት ጥያቄ ተሰቅለህ ነበር ወይም አልተሰቀልክም?" የሚል ነው - ከእስር የተለቀቁት አቶ ሐብታሙ አያሌው።

የቃለ ምልልሱን ሁለተኛውን ክፍል ከዚህ ያድምጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:19:06 0:00


የቀድሞው የተቃዋሚው አንድነት ፓርቲ ቃል አቀባይ በሽብር ወንጀል ተከሰው እሥር ቤት በቆዩባቸው ሁለት ዓመታት በምርመራ ሳቢያ ደረሰብኝ ያሉት ከባድ ስቃይ አሁን ለሚገኙበት የጤና ቀውስ እንደዳረጋቸው ይናገራሉ።

ወህኒ ቤቶች ውስጥ የሚፈጸሙ ጭካኔ የተሞላባቸው ልዩ ልዩ የምርመራ ዓይነቶች በአብዛኞቹ እሥረኞች ላይ ሕልፈትን ጨምሮ ለተመሳሳይ የጤና ችግሮች እንደሚዳርጉም አቶ ሃብታሙ ያስረዳሉ።

አቶ ሃብታሙ አያሌው በዚህ ፕሮግራም ላይ ስለ ምርመራ ዓይነቶች በዘረዘሩበት ወቅት የሰጡት ማብራሪያ እጅግ ዘግናኝ በመሆኑ ሕጻናት ልጆች እንዳያደምጡት የወላጆችን ትብብር እንጠይቃለን። አቶ ሃብታሙ አያሌውን ያነጋገራቸው የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ ሰሎሞን ክፍሌ ነው።

የቀድሞው የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው የ'ማዕከላዊ' ታሪኮች
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:27 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG