በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከጉራ ፈርዳ የተፈናቀሉ መታሠራቸውንና ገሚሶቹም ወደአምቦ መወሰዳቸውን መኢአድ ገለፀ


በቤንች ማጂ ዞን
በቤንች ማጂ ዞን

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል፤ በቤንች ማጂ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ የሚኖሩ፤ ከዓመታት በፊት ከአማራ ክልል የሄዱ ሠፋሪ አርሦ አደሮች በአካባቢው ባለሥልጣናት ተገድደው ቀያቸውን ልንዲለቅቁ እየተደረጉ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል።




please wait

No media source currently available

0:00 0:08:56 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


ከረዥም ጊዜ በፊት በአካባቢው እንዲሠፍሩ የተደረጉና አሁንም ድረስ በዚያው ነዋሪ የሆኑ አርሦ አደሮች የእርሻ መሬታችንን እንዳናርስና በማሣ ላይ እርሻ ያለበትን ጨምሮ በጨረታና በሃራጅ እየተሸጠባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይህንን የአርሦ አደሮቹን ክስ እና ደርሶብናል ወይም እየደረሰብን ነው የሚሏቸውን በደሎች እና እንግልቶች ከሌሎች ወገኖችንም ለማጣራትና በችግሩ ውስጥ አሉ የሚባሉ ወገኖች የሚሉትን ለማዳመጥ ብዙ ጥረቶችን እያደረግን እንገኛለን፡፡

ከእነዚህ መካከል የጉራ ፈርዳ ወረዳ አስተዳዳሪ፣ አቶ መሬሣ ጎዪ እና የወረዳው ፖሊስ አዛዥ አቶ ምሥክር ይገኙበታል፡፡ እነርሱን ለማግኘት በተከታታይና ለብዙ ጊዜ ሙከራ ቢደረግም ማግኘት አልተቻለም፡፡

ጉዳዩን በቅርብ እየተከታተልኩ ነው የሚለው የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ወንድማገኝ ደነቀ “የተፈናቀሉ ሰዎችን ስም ዝርዝር ሳይቀር ይዘናል፤ ሰዎቻችን እቦታው ድረስ ሄደው ሁኔታውን አይተዋል” ብለዋል፡፡

በመኪና እየተጫኑ ተወስደዋል ካሏቸው 150 የሚሆኑት ወደ ምዕራብ ሸዋ፣ አምቦ ከተማ መወሰዳቸውን፣ ሞባይል ስልኮቻቸውን መነጠቃቸውንና ያሉበትን ሁኔታ እንደማያውቁ ገልፀዋል፡፡ ሌሎቹ 200 ሰዎች ደግሞ በወረዳው ከተማ ሚዛን ተፈሪ እሥር ቤት ውስጥ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡

በሚፈናቀሉት ሰዎች ላይ ድብደባና ሌሎችም ጉዳቶች እንደደረሱባቸው፣ ጥይት እንደሚተኮስባቸው አቶ ወንድማገኝ አመልክተዋል፡፡

ዘገባውን ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG