በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራር አባል በ "ለጥያቄዎ መልስ" ዝግጅት ላይ


የአርበኞች ግንቦት ሰባት የዓለም አቀፍ አመራር የዉጭ ግንኙነት ሃላፊና የንቅናቄዉ ምክር ቤት አባል አቶ ነአምን ዘለቀ፣ በኢትዮጵያ ስልጣን ለመያዝ ሳይሆን በስልጣን ላይ ያለዉን መንግስት አስወግዶ አገሪቱን ለዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ለማመቻቸት ነዉ ብለዋል።

የአርበኞች ግንቦት ሰባት የዓለም አቀፍ አመራር የዉጭ ግንኙነት ሃላፊና የንቅናቄዉ ምክር ቤት አባል አቶ ነአምን ዘለቀን በዝግጅቱ ላይ ለአድማጮች በሰጡት መልስ የአገር አድን ጥምረት ንቅናቄ የተፈጠዉ በኢትዮጵያ ስልጣን ለመያዝ ሳይሆን በስልጣን ላይ ያለዉን መንግስት አስወግዶ አገሪቱን ለዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ለማመቻቸት ነዉ ብለዋል። በእርሳቸዉ አገላለጽ የድርጅታቸዉ ዋና የትግራይን ሕዝብ በማይወክሉ ባሉዋቸዉ ጥቂት የትግራይ ተወላጆች የተመሰረተ ኢዴሞክራሲያዊና አድሎኛ መንግስት ገርስሶ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለፍትሃዊ ስርዓት ማብቃት ነዉ። አብዛኛዉ የትግራይ ሕዝብ እንደተቀረዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ የስርዓቱ ሰለባ ነዉ ብለዋል የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራር አባል አቶ ነዓምን ዘለቀ።

በቀደሙት ዓመታት በጦርነት ተጎድታለች፥ ሕዝብ አልቋል ደህይቷል በሰላም ለምን አትታገሉም ሲሉ አድማጮች ላቀረቡት ጥያቄ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ መሪዎች በተደጋጋሚ ለቀረቡ የብሔራዊ እርቅ ጥሪዎች ፈቃደኞች ሆነዉ አልተገኙም ብለዋል አቶ ነዓምን።

ኤርትራ ካሁን ቀደም በድንበርዋ ዉስጥ ይንቀሳቀሱ የነበሩ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎችን አስራለች ግድላለች፥ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እንዲሰፍን አትተባበርም ይልቁንም አንድነትዋ እንዲበትን ትፈልጋለች እንዴት አስመራ ጋር ትተባበራላችሁ የሚሉ ጥያቄዎችም ቀርበዋል ከአድማጮች።

አቶ ነዓምን በሰጡት መልስ ኤርትራ ዉስጥ የታሰሩ ወይም የተገደሉ ኢትዮጵያዉያን የአገሪቱ ጸጥታ ላይ አደጋ የጋረጡ ናቸዉ የኤርትራ መንግስት ግን ሰላምና ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ኢትዮጵያ ዉስጥ እንዲሰፍን ይፈልጋል ብለዋል የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራር አባል አቶ ነዓምን ዘለቀ።

ሙሉዉን ዝግጅት የተያያዘዉን የሁለት ክፍል ድምጽ ፋይሎቻትችንን በመጫን ያድምጡ።

ክፍል 1፡ የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራር አባል በ "ለጥያቄዎ መልስ" ዝግጅት ላይ 15'29"
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:29 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
ክፍል 2፡ የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራር አባል በ "ለጥያቄዎ መልስ" ዝግጅት ላይ 23’54”
please wait

No media source currently available

0:00 0:23:53 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG