በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጀርመን እአአ 2015 ወደ 1.1 ሚልዮን ሰዎች በፍልሰተኛነት ድንበሯ ላይ መመዝገባቸውን ገለጸች

ፍልሰተኞች በበርሊን ጀርመን በሚገኘው ቢሮ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ተሰልፈው (ፎቶ ሮይተርስ/REUTERS)
ፍልሰተኞች በበርሊን ጀርመን በሚገኘው ቢሮ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ተሰልፈው (ፎቶ ሮይተርስ/REUTERS)

ጀርመን በየአመቱ የሚገቡ ፍልሰተኞች ከ2014 በአምስት እጥፍ ከፍ ያለ መሆኑንም ጀርመን አመልክታለች።

ጀርመን፣ ባለፈው ዓመት (2014 መኾኑ ነው) ወደ 1.1 ሚልዮን (Million) ሰዎች በፍልሰተኛነት ድንበሯ ላይ መመዝገባቸውን ገለጸች።

ጀርመን ዛሬ ረቡዕ ይህንኑ በአኃዝ ስታስቀምጥ፣ 428,468 ሰዎች የሦርያውን የርስ በርስ ጦርነት በመሸሽ የፈለሱ ሲሆኑ፣ ይህም ወደ ጀርመን ከገቡት መካከል ከፍተኛውን ቁጥን የያዘ መሆኑ ተመልክቷል።

ቀጣዮቹ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሁለት አገሮች፣ በተመሳሳይ የርስ በርስ ጦርነት በመሸሽ ወደ ጀርመን የፈለሱ፣ ከአፍጋኒስታን 154,046 እንዲሁም ከኢራቅ 121,662 ናቸው።

በየአመቱ የሚገቡ ፍልሰተኞች ከ2014 በአምስት እጥፍ ከፍ ያለ መሆኑንም ጀርመን አመልክታለች። የዜና ዘገባውን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

ጀርመን እአአ 2015 ወደ 1.1 ሚልዮን ሰዎች በፍልሰተኛነት ድንበሯ ላይ መመዝገባቸውን ገለጸች
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:02 0:00

XS
SM
MD
LG