አዲስ አበባ —
ህክምናው በዘገየ ቁጥር በሽታው ወደ ሌላ ደረጃ ሊያድግ እንደሚችል እና ለህክምናም እጅግ አስቸጋሪ እንደሚሆን ሃኪሞች መናገራቸውን የቤተሰቡ ምንጮች ተናግረዋል።
አቶ ሀብታሙ አያሌው የፈደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ቀደም ሲል ካቀረበው የሃኪም ማስረጃ በተጨማሪ የህክምና ቦርድ አባላት የፈረሙበት እና ታማሚው በግድ ወደ ውጭ ወጥቶ መታከም እንዳለበት የሚያረጋገጥ ማስረጃ እንዲያቀርብ በሰጠው ትእዛዝ መሰረት ይህን ማስረጃ ዛሬ ማግኘቱን የቅርብ ጓደኛው አቶ ዳኒኤል ስበሺ እና ቤተሰቡ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።