በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መንገዶች ለምን በጎርፍ ይሰነጠቃሉ?ለምንስ ይዘጋጋሉ?


በ1998 በድሬደዋ ያጋጠመው ጎርፍ በከተማ መግቢያ ገነት መናፈሻ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ አስፓልቱን ቆርጦት
በ1998 በድሬደዋ ያጋጠመው ጎርፍ በከተማ መግቢያ ገነት መናፈሻ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ አስፓልቱን ቆርጦት

በኢትዮጵያ የተለያዩ ከፍሎች እየዘነበ ያለው ዝናብ በመሠረት ልማት ላይም አደጋ እያደረሰ መኾኑ እየተነገረ ነው። ዝናብ ሲዘንብ ለምን መንገዶች በጎርፍ ይዘጋጋሉ? ለምንስ ይሰነጠቃሉ? መንገዶቹ ሲሠሩ ለምን አስቀደሞ የጎርፉ ሁኔታ ከግምት ውስጥ አይገባም? ለኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሳምሶን ወንድሙ የቀረበላቸው ጥያቄ ነው። ጽዮን ግርማ አቶ ሳምሶን ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ እንዲሰጡ ጠይቃቸዋለች።

በኤልኒኖ ምክንያት በተከሰተው ድርቅና በተከታታይ በቂ ዝናብ አለመዝነቡን ተከትሎ በኢትዮጵያ ከ10. 2 ሚሊዮን ዜጎች በላይ በድርቅ ምክንያት ለተረጂነት ተጋልጠዋል። የድርቅ ወራቱ እንዳለፈ ደግሞ በሀገሪቱ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ሰሞኑን በተከሰተ የጎርፍ መጥለቅለቅ እና የመሬት መደርመስ ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት እስከ አርብ ግንቦት አምስት ቀን ድረስ በአጠቃላይ የ92 ሰው ሕይወት ጠፍቷል። 86,000 ሰው ተፈናቅሏል። ከዚህ በኋላም ወደ 400 ሺህ ሰው ሊፈናቀል እንደሚችል እየተነገረ ነው።

ከዚህ በተጨማሪም ጎርፉ መሠረት ልማት ላይም አደጋ እያደረሰ መኾኑ እየተነገረ ነው። በሰሞኑ ዝናብ በወላይታ 18 ሜትር ርዝመትና ሦስት ሜትር ስፋት ያለው የመንገድ መሰንጠቅ አስከትሏል። ከሞጆ ወደ ሐዋሳ በሚወስደው መንገድ ላይ በመቂ፣ በአሰላ፣በሸዋ ሮቢት፣ በጂግጂጋ፣ በድሬደዋ ፣በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች በዝናብ ጊዜ መንገዶቹ በጎርፍ ይጥለቀለቃሉ፣ይሰነጠቃሉ እንዲሁም ድልድዮች ይሠበራሉ።

ዝናብ ሲዘንብ ለምን መንገዶች በጎርፍ ይዘጋጋሉ? ለምንስ ይሰነጠቃሉ? መንገዶቹ ሲሠሩ ለምን አስቀደሞ የጎርፉ ሁኔታ ከግምት ውስጥ አይገባም? ለኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሳምሶን ወንድሙ የቀረበላቸው ጥያቄ ነው።

ጽዮን ግርማ አቶ ሳምሶን ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ እንዲሰጡ ጠይቃቸዋለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

መንገዶች ለምን በጎርፍ ይሰነጠቃሉ?ለምንስ ይዘጋጋሉ?
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:52 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG