በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአዳማ ከተማ በደረሰ የጎርፍ አደጋ 4,500 ሰዎች ተፈናቀሉ


አዳማ ከተማ
አዳማ ከተማ

በአዳማ ከተማ ከትናንት በስቲያ ለሊት በደረሰው ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ የተፈናቃዮች ቁጥር 4,500 መድረሱ ተነገረ። የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የከተማው ነዋሪዎች፤በጎርፍ አደጋው ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው መጠለያ ማጣቸውን ይናገራሉ።

በአሁኑ ሰዓትም ዘመድ ያለው በየዘመድ አዝማዱና ጓደኛው ቤት እየተጠለለ መሆኑን ገልጸው መጠጊያ የሌላቸው ሰዎች ግን ውጭ ሜዳ ላይ እና ጎርፉ ባለበት አካባቢ ለማደር መገደዳቸውን ይገልፃሉ።

በአሁኑ ሰዓትም በቂ እርዳታ እየተሰጣቸው እንዳልሆነ ጠቁመው ቀድሞውኑ በከተማው በቂ የጎርፍ ማስተላለፊያ ቱቦ ቢሠራ ኖሮ ከእንዲህ ያለ አደጋ ሊተርፉ ይችሉ እንደነበር አስረድተዋል።

የአዳማ ከተማ የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀቢብ ቃሲም ስለጉዳዩ ተጠይቀው አደጋው በተፈጠሮ የመጣ እንደሆን ገልፀው፤ በአሁኑ ሰዓት የተፈናቀሉትን 4,500 ሰዎች ለመርዳት ሦስት የመርጃ ጣቢያዎች አቋቁመው እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የዘጠኝ ወር ነፍሰጡር መሆኗን የገለፀችልን ወ/ሮ ቢሊሱማ ሁሴን ቤቷ በጎርፉ በመጠረጉና መጠለያ ባለማግኘቷ ዛፍ ስር ማደሯን ተናግራለች።

በዚህ ጎርፍ ሁለት የጎዳና ተዳዳሪዎች መወሰዳቸውን ነዋሪዎችን ጠቅሰን በትናንትናው ዕለት መዘገባችን ይታወሳል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

በአዳማ ከተማ በደረሰ የጎርፍ አደጋ 4,500 ሰዎች ተፈናቀሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:33 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


XS
SM
MD
LG