በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲሱ የፊፋ ፕሬዘዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ አፍሪካን ሲጎበኙ የመጀመሪያ ምርጫቸው ደቡብ ሱዳን ሆናለች


ፋይል ፎቶ - የፊፋ አዲስ ፕረዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ከደቡብ ሱዳን ምክትል ፕረዚደንት ጄምስ ዋኒ ኢጋ ጋር በጂባ
ፋይል ፎቶ - የፊፋ አዲስ ፕረዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ከደቡብ ሱዳን ምክትል ፕረዚደንት ጄምስ ዋኒ ኢጋ ጋር በጂባ

ጂያኒ ዛሬ ጁባ ውስጥ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፥ በሃገሪቱ የእግር ኳስ ስፖርትን ደረጃ ከፍ ለማድረግ፥ ቢሮአቸው ከደቡብ ሱዳን የስፖርቱ ባለሥልጣናት ጋር በቅርበት ይሠራል ብለዋል።

ከሦስት ሳምንታት በፊት የተመረጡት አዲሱ የፊፋ ፕሬዘዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ (Gianni Infantino) አፍሪካን ሲጎበኙ የመጀመሪያ ምርጫቸው ደቡብ ሱዳን ሆናለች።

ጂያኒ (Gianni) ዛሬ ጁባ ውስጥ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፥ በሃገሪቱ የእግር ኳስ ስፖርትን ደረጃ ከፍ ለማድረግ፥ ቢሮአቸው ከደቡብ ሱዳን የስፖርቱ ባለሥልጣናት ጋር በቅርበት ይሠራል ብለዋል።

የፊፋው ባለሥልጣን ወደ ጁባ የመጡትም ደቡብ ሱዳን ከቤኒን ጋር የምታደርገውን ግጥሚያ ለመመልከት መሆኑን አስረድተዋል። በጨዋታው ቤኒን 2 ለ 1 አሸንፋለች።

አዲሱ የፊፋ መሪ ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በጉብኝታቸው ወቅት ከፕሬዘዳንት ሳልቫ ኪር (Salva Kiir) ጋር ተገናኝተው በስፖርቱ ዙሪያ ተነጋግረዋል ተብሏል።

ጂያኒ ደቡብ ሱዳንን ሲጎበኙ ይህ ሁለተኛ ጊዜአቸው ሲሆን ከአንድ ወር በፊትም የምረጡኝ ዘመቻቸውን ሲያካሂዱ የሃገሪቱን ድጋፍ ለማግኘት ጁባ እንደነበሩ ተዘግቧል።

XS
SM
MD
LG