በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዓለም እጅግ የወደቁ መንግሥታትን አስመልክቶ የተካሄደ ውይይት


በዓለም ካሉ፥ የአስተዳደር ድክመት እጅግ ከበረታባቸው 56 ሀገሮች ኢትዮጵያን በ 17ኛነት ያሰፈረው አንድ በዩናይትድ ስቴትስ እየታተመ የሚወጣ የፖሊሲ መጽሔት ኤርትራ በብዙ እንደምትሻልና በረድፉ ውስጥ 30ኛ መሆኗን እንዳስታወቀ በትላንት ምሽት የዜና ፕሮግራማችን ላይ መገለጹ ይታወሳል።

በዓለም እጅግ የወደቁ መንግሥታት /Most Failed States/ የሚለውን ዝርዝር መጽሔቱ በአራተኛ ዓመታዊ እትሙ ያወጣው፥ ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ያስመዘገቧቸውን እርምጃዎች ገምግሞ መሆኑ ተገልጿል።

ይኸው «የውጭ ፖሊሲ» የተሰኘው በዋሺንግተን ፖስት ጋዜጣና ኒውስዊክ መጽሔት ጥምር መምሪያ የሚወጣው ሕትመት፥ ኢትዮጵያን ከበርማ ቀጥሎ እጅግ የተዳከመ መንግሥታዊ አስተዳደር ያለባት ሀገር መሆኗን አስፍሮ፥ ሰሜን ኰሪያ ደግሞ ከኢትዮጵያ በሁለት ደረጃዎች እንደምትሻል ጽፏል።

ከባሱት የባሱ አምባገነን ሲልም በዘጠነኛነት የመደባቸውን የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ከቀድሞው ማርክሲስት ወታደራዊ መሪ ከኰለኔል መንግሥቱ የባሱ፥ ተቃዋሚዎችን በሙሉ ያፈኑና ምርጫዎችንም ያጭበረበሩ ናቸው ብሏል።

ሰሎሞን ክፍሌ በቀጣዩ «ዲሞክራሲ በተግባር» ፕሮግራሙ ባለሞያ ጋብዞ፥ እጅግ የወደቁ መንግሥታት ማለት ምን ማለት ነው ለሚለውና ለሌሎች በፖሊሲው መጽሔት የተዘረዘሩ አንዳንድ ነጥቦች ማብራሪያ አግኝቷል።

እንግዳው አቶ ጁዋር መሃመድ ይባላሉ። የስታንፈርድ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅና ገለልተኛ የፖለቲካ ተንታኝ ናቸው።

ውይይቱን ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG