በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ሕብረት መሪዎች ብራሰልስ ውስጥ በፍልሰተኞች ጉዳይ ላይ ስብሰባ እያካሄዱ ነው


የቱርክ ምክትል ሚኒስትር አህመት ዳቮትጉሉ በአውሮባ ሕብረት ስብሰባ ላይ
የቱርክ ምክትል ሚኒስትር አህመት ዳቮትጉሉ በአውሮባ ሕብረት ስብሰባ ላይ

የአውሮፓ ሕብረት በአጠቃላይ እስከ 70,000 የሚሆኑ ስደተኞችን ተቀብሎ እንደሚያስፍር ገለጿል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች አገልግሎት ሂደቱን ይከታተለዋል።

የአውሮፓ ሕብረት መሪዎች ብራሰልስ ውስጥ በሚያካሄድ የሁለት ቀናት ስብሰባ ወደ አውሮፓ ስለሚፈልሱት ሰዎች ጉዳይ ስምምነት እንዲያደርጉ ይጠበቃል።

ጉባኤው የሚነጋገርበት ነጥብ በአውሮፓ ሕብረት ምስራቃዊ ጫፍ ባሉት ሀገሮች ላይ የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ ሲባል በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልሰተኞችን መልሶ ወደ ቱርክ ስለመላክ ጉዳይ ነው።

ቱርክ ለምትቀበለው እያንዳንዱ ሕጋዊ ፈቃድ የሌለው መጤ ልዋጭ የአውሮፓ ሕብረት አንድ ሶርያዊ ስደተኛን ከቱርክ ትወስዳለች። የአውሮፓ ሕብረት በአጠቃላይ እስከ 70,000 የሚሆኑ ስደተኞችን ተቀብሎ እንደሚያስፍር ገለጿል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች አገልግሎት ሂደቱን ይከታተለዋል።

አንድ የሰብአዊ መብት ቡድን ግን የአውሮፓ ሕብረት ስምምነትር ላይ ከመድረሱ በፊት ሕብረቱ ስደተኞችን እንዳይቀያየር ጥሪ አቅርቧል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል የአውሮፓ ሕብረት በተሰበሰበበት ህንጻ ፊት ሆኖ ተቃውሞ አሰምቷል። የአውሮፓ ሕብረት በሰው ህይወት ላይ መቸርቸር የለብትም ሲሉ የአምነስቲ የአውሮፓ ክፍል ስራ-አስኪያጅ ፎቲስ ፊሊፖ አስገንዝበዋል።

በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ፍልሰተኞችን ከአውሮፓ ሕብረት ወደ ቱርክ ለማዘዋወር (ቱርክና በአውሮፓ ሕብረት) የሚያካሂዱት ድርድር ምን አንደምታ ሊኖረው እንደሚችል፣ የሰብዓዊ መብት አስከባሪ ቡድኖች እየተነጋገሩበት ነው። በዛሬው ዕለት የቀጠለው ውጥረት የተመላበት ድርድር ከተካሄደ በኋላ፣ ቱርክና የአውሮፓ ሕብረት የፍልሰተኞችን መጉረፍ ለመገደብ ስምምነት የደረሱ ቢመስልም፣ ስምምነቱ ተግባራዊ ከመሆን ይልቅ የሕግ ጥያቄ ሊያስነሳ እንደሚችል ተመልክቷል።

ባለፈው ዓመት ከ1.2 ሚልዮን በላይ ስደተኞችንና ፍልሰተኞችን ያስተናገደው የአውሮፓ ሕብረት፣ በአጠቃላይ የስደተኞችን ቀውስ ለመግታት እየሞከረ መሆኑ ታውቋል።

XS
SM
MD
LG