በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ ምርጫ እስካሁን የጎላ ችግር እንዳልታየ የአውሮፓ ህብረት ገለጸ

ሂደቱ እንደ ምርጫ 97 የተሟሟቀ እንዳልሆነ ተስ በርማን ተናግረዋል

የኢትዮጵያ ብሄራዊው የምርጫ ቦርድ ለአርባ ሶስት ሺህ የምርጫ ጣቢያዎች
የሚያስፈልጉ የምርጫ ቁሶችን ለማቅረብ የሚችለውን ሁሉ እያደረገ ነው ሲሉ
በኢትዮጽያ የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች ሃላፊ ተስ በርማን ተናገሩ።

ተስ በርማን የኢትዮጵያን ምርጫ የሚከታተሉት የአውሮፓ ህብረት የረዥም ጊዜ
ታዛቢዎች ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በመላ ሀገሪቱ ሲዘዋወሩ ቆይተዋል። የአጭር
ጊዜ ታዛቢዎቹ ደግሞ አሁን ከአዲስ አበባ ወጥተው እየተንቀሳቀሱ ነው ብለዋል።

“ከአምስት አመታት በፊት ከተከሄደው ምርጫ ጋር ሲወዳደር የያኔውን ያህል
የተሟሟቀ አይመስልም። ክርክሮቹ ግን ሞቅ ያሉ ናቸው። አንዳንዴ የእርስበርስ
መካሰስ ቢኖርም ሁሉም ወገኖች ባለፈው ምርጫ የታየው ግጭት እንዲደገም
የሚፈልጉ አይመስለኝም። በሌላ በኩል ደግሞ የሚሰነዘሩት መወጃጀሎች ከወዳጃዊ
መንፈስ የራቁ ናቸው።” ይላሉ በርማን።

የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች ሃላፊ አያይዘውም “እዚህ ያለነው፣ የዚህ
አመቱን ምርጫ ለመታዘብ እንጂ ያለፈውን ለመዳሰስ ስላልሆነ የምናተኩረው
በዚህ አመቱ ምርጫ ላይ ነው። ተግባራችን የሚመሰረተውም በሚሰሙ
ክሶችና አስተያየቶች ላይ ሳይሆን በቦታው ላይ ባለው ሀቅና ሊጣሩ በሚችሉ
ነገሮች ላይ ይሆናል” በማለት በርማን አስረድተዋል።

XS
SM
MD
LG