በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጎንደርና የደብረ ማርቆስ አድማዎች


የኢትዮጵያ ካርታ
የኢትዮጵያ ካርታ

በጎንደርና በደብረማርቆስ ከተሞች የሥራ ማቆም አድማ ተመትቷል፡፡

የጎንደርና የደብረ ማርቆስ አድማዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:32:19 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በጎንደርና በደብረማርቆስ ከተሞች የሥራ ማቆም አድማ ተመትቷል፡፡

በከተሞቹ ዛሬ ንግዶችና የመንግሥትን ጨምሮ መሥሪያ ቤቶች ዝግ ሆነው መዋላቸውን የየአካባቢው ነዋሪዎችና የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድ ገልፀዋል፡፡

በምሥራቅ አማራም በወልድያ፣ በዋድላ፣ በመቄት፣ በላሊበላና ሌሎችም አካባቢዎች የተጠናከረ የፀጥታ ኃይሎች እንቅስቃሴ እንደሚታይና ሰዎችም እየታሠሩ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

አድማውን የጠራው ማን እንደሆነ ተለይቶ እንደማይታወቅ መኢአድም ያነጋገርናቸው ሌሎች አካላትም ተናግረዋል፡፡

አድማው እስከነገ እንደሚቀጥል ተሰምቷል፡፡

ጎንደርና ደብረ ማርቆስ ላይ አገልግሎት ሰጭዎች ትናንትና ዛሬ ዘግተው መዋላቸውን የክልሉ መንግሥት የኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ለቪኦኤ በሰጡት ማብራሪያ ተናግረዋል፡፡

ባሕር ዳር ላይ ችግር እንደሌለ፣ በአጠቃላይ የክልሉ ሁኔታም እየተረጋጋ መሆኑንም አቶ ንጉሡ አመልክተዋል፡፡

ለሙሉው ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG