በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮ-ቴሌኮም ከቀድሞ የቴሌ ሰራተኞች የሚያስቀረው ሲሶውን ነው


ሰራተኞች ደሞዝ እየተከፈላቸው ቢሮ ቢውሉም መቀነሳቸው ተነግሯቸዋል

የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌኮሚውኒኬሽን ኮርፖሬሽን ሰራተኞች አመራሩ በፈረንሳይ ኩባንያ አስተዳድር ከተዛወረ ወዲህ፤ ሶስት አራተኛው መቀነሳቸውንና የወደፊት እጣ ፋንታቸው እንደማይታወቅ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ቴሌኮሚውኒኬሽን ኮርፖሬሽን በአዋጅ ፈርሶ፤ ስሙ ኢትዮ-ቴሌኮም እንዲባልና አስተዳደሩም በፈረንሳዩ የቴሌኮም ኩባንያ ስር እንዲሆን ከተደረገ ወራት አልፈዋል።

በቀድሞው ቴሌ ያገለግሉ ከነበሩት ሰራተኞች መካከል በስራ ገበታቸው የሚቆዩት ሲሶው ብቻ መሆናቸውን ሰራተኞቹ ይናገራሉ።

በእርግጥ በአሁኑ ሰዓት ሙሉ ደመወዛቸው እየተከፈላቸው፤ በስራ ገበታቸው እንደሚገኙ የገለጹት ሰራተኞች፤ መቀነሳቸው ተነግሯቸዋል።

የሚቀረውንና በሚባረረውን ሰራተኛ ለመለየት የተወሰዱት መስፈርቶች ፍትሃዊና በችሎታና በአገልግሎት ላይ ያተኮሩ አለመሆናቸውን ለአሜሪካ ድምጽ አስተያየታቸውን የሰጡ ተቀናሽ ሰራተኞች አብራርተዋል።

የአዲስ አበባው ዘጋቢ እስክንድር ፍሬው ሰራተኞቹን አነጋግሮ ያጠናቀረውን ዘገባ ያዳምጡ።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG