በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ አሜሪካዊያን ሠልፍ በዓለም ባንክ አደረጉ


የኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ አሜሪካዊያን ሠልፍ በዓለም ባንክ
የኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ አሜሪካዊያን ሠልፍ በዓለም ባንክ



please wait

No media source currently available

0:00 0:08:34 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የዓለም ባንክ በልማት ስም ለኢትዮጵያ መንግሥት የሚሰጠው ዕርዳታ ለጥፋትና ለሕዝብ ማፈናቀያ ውሏል የሚሉ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ አሜሪካዊያን ቅዳሜ ሚያዝያ 12/2005 ዓ.ም ዋሽንግተን ዲ.ሲ. ውስጥ በሚገኘው የዓለም ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰላማዊ ሠልፍ አድርገዋል።

ሰልፈኛው ቀኑን የመረጠውም የዓለም ባንክ ለአፍሪቃ የሚሰጠውን እርዳታ ለመገምገም በዕለቱ ስብሰባ ስለሚያደርግ በመሆኑ እንደሆነ የሠልፉ አስተባባሪዎች ለቪኦኤ ገልፀዋል።

“ሀፍረት ለዓለም ባንክ! የዓለም ባንክ የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ መርዳቱን ያቁም!” የሚሉና መሰል መፈክሮች በእንግሊዝኛ ተስተጋብተዋል።

ወደ አዳራሽ ለሚገቡ ተሰብሳቢዎችም የሰልፉ አስተባባሪዎች በኢትዮጵያ አለ የሚሉትን የመብቶች ረገጣ የሚገልፅ በፎቶግራፍ የተደገፈ በራሪ ወረቀት ከማደላቸውም በላይ ዓለምአቀፍ ስምምነት የደረሰባቸው ሰብዓዊ መብቶች እስካልተከበሩ ድረስ «ዓለማችን ከድኅነት የፀዳች ትሆናለች» የሚለውን የባንኩን ፕሬዚደንት የጂም ዮንግ ኪምን ራዕይ እውን ማድረግ ከቶ አይቻልም በማለት በበራሪው ወረቀት ላይ በጉልህ ማስፈራቸውም ተስተውሏል።

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ መንግሥት የሚሰጠውን እርዳታ እንዲያቆም በተጠራው በዚሁ የቅዳሜ ሠልፍ ላይ የተለያዩ የፖለቲካ፣ የማኅበራዊ፣ የሲቪክና የሃይማኖት ድርጅቶች ተወካዮች መካፈላቸውን የገለፀው የአዲሱ አበበ ዘገባ የአስተባባሪዎቹንና የተሣታፊዎችንም አስተያየቶች ይዟል፤ ያዳምጡት፡፡
XS
SM
MD
LG