በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ቤተሰቦቻችን ስንቅ አንቀበልም አሉን"- የእስረኛ ቤተሰቦች


በቀለ ገርባ
በቀለ ገርባ

የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ እና የፓርቲው ፀሐፊ አቶ ደጀኔ ጣፋ ቤተሰቦች እስረኛ ቤተሰቦቻቸው በማርሚያ ቤቱ ውስጥ ለእስረኛ የሚሰጥ መብት ለእነሱ ስለተነፈጋቸው ማረሚያ ቤቱ መብታቸውን እስኪያከብርና ውሳኔ እስኪሰጣቸው ምግብ እንደማይቀበሉ እንደነገሯቸው ተናገሩ።

በቂልንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ የእስረኛ ቤተሰቦች ታሳሪ ቤተሰቦቻቸውን አግኝተው ምግብ ማቀበል እንዳልቻሉና ሲያገኟቸውም ማረሚያ ቤቱ ውስጥ ከፍተኛ ችግር ስላለባቸው ችግራቸው እስኪፈታ ምግብ እንደማይቀበሏቸው እንደነገሯቸው ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ።

የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ልጅ ወ/ት ቦንቱ በቀለና የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ደጀኔ ጣፋ ባለቤት ወ/ሮ አሰለፈች ሙላት ዛሬ ወስደውት የነበረውን ስንቅ ይዘውት ወደቤት እንደተመለሱ ሲናገሩ የሕግ ጠበቃቸው ደግሞ ደንበኞቻቸውን ማግኘት እንዳልቻሉ ተናግረዋል።

ጽዮን ግርማ ዝርዝር አላት።

"ቤተሰቦቻችን ስንቅ አንቀበልም አሉን"- የእስረኛ ቤተሰቦች
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:27 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG